87) Sūrat Al-'`lá

Printed format

87) سُورَة الأعلَى

Sabbiĥi Asma Rabbika Al-'A`lá 087-001 ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡ سَبِّحِ ا‍سْمَ رَبِّكَ ا‍لأَعْلَى
Al-Ladhī Khalaqa Fasawwá 087-002 የዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡ ا‍لَّذِي خَلَقَ فَسَوَّى
Wa Al-Ladhī Qaddara Fahadá 087-003 የዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡ وَالَّذِي قَدَّرَ فَهَدَى
Wa Al-Ladhī 'Akhraja Al-Mar`á 087-004 የዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡ وَالَّذِي أَخْرَجَ ا‍لْمَرْعَى
Faja`alahu Ghuthā'an 'Aĥwá 087-005 (ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡ فَجَعَلَهُ غُث‍‍َ‍ا‍ءً أَحْوَى
Sanuqri'uka Falā Tan 087-006 (ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡ سَنُ‍‍ق‍‍ْ‍‍ر‍‍ِئُكَ فَلاَ تَ‍‍ن‍سَى
'Illā Mā Shā'a Al-Lahu 'Innahu Ya`lamu Al-Jahra Wa Mā Yakh 087-007 አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡ إِلاَّ مَا ش‍‍َ‍ا‍ءَ ا‍للَّهُ إِ‍نّ‍‍َهُ يَعْلَمُ ا‍لْجَهْرَ وَمَا يَخْفَى
Wa Nuyassiruka Lilyusrá 087-008 ለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡ وَنُيَسِّرُكَ لِلْيُسْرَى
Fadhakkir 'In Nafa`ati Adh-Dhikrá 087-009 ግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡ فَذَكِّرْ إِ‍ن‍ْ نَفَعَتِ ا‍لذِّكْرَى
Sayadhdhakkaru Man Yakhshá 087-010 (አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡ سَيَذَّكَّرُ مَ‍‍ن‍ْ يَخْشَى
Wa Yatajannabuhā Al-'Ashqá 087-011 መናጢውም ይርቃታል፡፡ وَيَتَجَ‍‍ن‍ّ‍‍َبُهَا ا‍لأَشْقَى
Al-Ladhī Yaşlá An-Nāra Al-Kub 087-012 ያ ታላቂቱን እሳት የሚገባው፡፡ ا‍لَّذِي يَصْلَى ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َ‍ا‍رَ ا‍لْكُ‍‍ب‍‍ْرَى
Thumma Lā Yamūtu Fīhā Wa Lā Yaĥyā 087-013 ከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም ሕያውም አይኾንም፡፡ ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ لاَ يَم‍‍ُ‍و‍تُ فِيهَا وَلاَ يَحْيَا
Qad 'Aflaĥa Man Tazakká 087-014 የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡ قَ‍‍د‍ْ أَفْلَحَ مَ‍‍ن‍ْ تَزَكَّى
Wa Dhakara Asma Rabbihi Faşallá 087-015 የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡ وَذَكَرَ ا‍سْمَ رَبِّهِ فَصَلَّى
Bal Tu'uthirūna Al-Ĥayāata Ad-Dun 087-016 ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡ بَلْ تُؤْثِر‍ُو‍نَ ا‍لْحَي‍‍َ‍ا‍ةَ ا‍لدُّ‍‍ن‍‍ْيَا
Wa Al-'Ākhiratu Khayrun Wa 'Abqá 087-017 መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡ وَالآخِرَةُ خَيْر‍ٌ وَأَ‍ب‍‍ْقَى
'Inna Hādhā Lafī Aş-Şuĥufi Al-'Ū 087-018 ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡ إِ‍نّ‍‍َ هَذَا لَفِي ا‍لصُّحُفِ ا‍لأ‍ُ‍ولَى
Şuĥufi 'Ibrāhīma Wa Mūsá 087-019 በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡ صُحُفِ إِ‍ب‍‍ْرَاه‍‍ِ‍ي‍مَ وَمُوسَى
Next Sūrah