88) Sūrat Al-Ghāshiyah

Printed format

88) سُورَة الْغَاشِيَه

Hal 'Atāka Ĥadīthu Al-Ghāshiyahi 088-001 የሸፋኝቱ (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን? هَلْ أَت‍‍َ‍ا‍كَ حَد‍ِي‍ثُ ا‍لْغَاشِيَةِ
Wujūhun Yawma'idhin Khāshi`ahun 088-002 ፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው፡፡ وُج‍‍ُ‍و‍ه‍‍‍ٌ يَوْمَئِذٍ خَاشِعَة‍‍‍ٌ
`Āmilatun Nāşibahun 088-003 ሠሪዎች ለፊዎች ናቸው፡፡ عَامِلَة‍‍‍ٌ نَاصِبَة‍‍‍ٌ
Taşlá Nārāan Ĥāmiyahan 088-004 ተኳሳን እሳት ይገባሉ፡፡ تَصْلَى نَاراً حَامِيَة‍‍‍ً
Tusqá Min `Aynin 'Āniyahin 088-005 በጣም ከፈላች ምንጭ ይጋታሉ፡፡ تُسْقَى مِنْ عَيْن‍‍‍ٍ آنِيَة‍‍‍ٍ
Laysa Lahum Ţa`āmun 'Illā Min Đarī`in 088-006 ለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡ لَيْسَ لَهُمْ طَع‍‍َ‍ا‍م‍‍‍ٌ إِلاَّ مِ‍‍ن‍ْ ضَ‍‍ر‍‍ِي‍ع‍‍‍ٍ
Lā Yusminu Wa Lā Yughnī Min Jū`in 088-007 የማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡ لاَ يُسْمِنُ وَلاَ يُغْنِي مِ‍‍ن‍ْ ج‍‍ُ‍و‍ع‍‍‍ٍ
Wujūhun Yawma'idhin Nā`imahun 088-008 ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው፡፡ وُج‍‍ُ‍و‍ه‍‍‍ٌ يَوْمَئِذ‍ٍ نَاعِمَة‍‍‍ٌ
Lisa`yihā Rāđiyahun 088-009 ለሥራቸው ተደሳቾች ናቸው፡፡ لِسَعْيِهَا رَاضِيَة‍‍‍ٌ
Fī Jannatin `Āliyahin 088-010 በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው፡፡ فِي جَ‍‍ن‍ّ‍‍َةٍ عَالِيَة‍‍‍ٍ
Lā Tasma`u Fīhā Lāghiyahan 088-011 በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡ لاَ تَسْمَعُ فِيهَا لاَغِيَة‍‍‍ً
Fīhā `Aynunriyahun 088-012 በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አልሉ፡፡ فِيهَا عَيْن‍‍‍ٌ جَا‍ر‍‍ِيَة‍‍‍ٌ
Fīhā Sururun Marfū`ahun 088-013 በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አልሉ፡፡ فِيهَا سُرُر‍ٌ مَرْفُوعَة‍‍‍ٌ
Wa 'Akwābun Mawđū`ahun 088-014 በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም፡፡ وَأَكْو‍َا‍ب‍‍‍ٌ مَوْضُوعَة‍‍‍ٌ
Wa Namāriqu Maşfūfahun 088-015 የተደረደሩ መከዳዎችም፡፡ وَنَمَا‍ر‍‍ِقُ مَصْفُوفَة‍‍‍ٌ
Wa Zarābīyu Mabthūthahun 088-016 የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አልሉ)፡፡ وَزَرَابِيُّ مَ‍‍ب‍‍ْثُوثَة‍‍‍ٌ
'Afalā Yanžurūna 'Ilá Al-'Ibili Kayfa Khuliqat 088-017 (ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች! أَفَلاَ يَ‍‍ن‍‍ْظُر‍ُو‍نَ إِلَى ا‍لإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ
Wa 'Ilá As-Samā'i Kayfa Rufi`at 088-018 ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች! وَإِلَى ا‍لسَّم‍‍َ‍ا‍ءِ كَيْفَ رُفِعَتْ
Wa 'Ilá Al-Jibāli Kayfa Nuşibat 088-019 ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ! وَإِلَى ا‍لْجِب‍‍َ‍ا‍لِ كَيْفَ نُصِبَتْ
Wa 'Ilá Al-'Arđi Kayfa Suţiĥat 088-020 ወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?) وَإِلَى ا‍لأَرْضِ كَيْفَ سُطِحَتْ
Fadhakkir 'Innamā 'Anta Mudhakkirun 088-021 አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና፡፡ فَذَكِّرْ إِ‍نّ‍‍َمَ‍‍ا‍ أَ‍ن‍‍ْتَ مُذَكِّر‍ٌ
Lasta `Alayhim Bimusayţirin 088-022 በእነርሱ ላይ ተሿሚ (አስገዳጅ) አይደለህም፡፡ لَسْتَ عَلَيْهِ‍‍م‍ْ بِمُسَيْطِر‍ٍ
'Illā Man Tawallá Wa Kafara 088-023 ግን (ከእውነት) የዞረና የካደ ሰው፤ إِلاَّ مَ‍‍ن‍ْ تَوَلَّى وَكَفَرَ
Fayu`adhdhibuhu Al-Lahu Al-`Adhāba Al-'Akbara 088-024 አላህ ታላቁን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡ فَيُعَذِّبُهُ ا‍للَّهُ ا‍لْعَذ‍َا‍بَ ا‍لأَكْبَرَ
'Inna 'Ilaynā 'Īābahum 088-025 መመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው፡፡ إِ‍نّ‍‍َ إِلَيْنَ‍‍ا إِيَابَهُمْ
Thumma 'Inna `Alaynā Ĥisābahum 088-026 ከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡ ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ إِ‍نّ‍‍َ عَلَيْنَا حِسَابَهُمْ
Next Sūrah