Nūn Wa Al-Qalami Wa Mā Yasţurūna | 068-001 ነ.(ኑን)፤ በብርእ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት፡፡ | نُون وَالْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَ |
Mā 'Anta Bini`mati Rabbika Bimajnūnin | 068-002 አንተ በጌታህ ጸጋ የተጎናጸፍክ ስትኾን ዕብድ አይደለህም፡፡ | مَا أَنْتَ بِنِعْمَةِ رَبِّكَ بِمَجْنُونٍ |
Wa 'Inna Laka La'ajrāan Ghayra Mamnūnin | 068-003 ላንተም (ከጌታህ) የማይቋረጥ ዋጋ በእርግጥ አልለህ፡፡ | وَإِنَّ لَكَ لَأَجْراً غَيْرَ مَمْنُونٍ |
Wa 'Innaka La`alá Khuluqin `Ažīmin | 068-004 አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ፡፡ | وَإِنَّكَ لَعَلى خُلُقٍ عَظِيمٍ |
Fasatubşiru Wa Yubşirūna | 068-005 ወደፊትም ታያለህ፤ ያያሉም፡፡ | فَسَتُبْصِرُ وَيُبْصِرُونَ |
Bi'ayyyikumu Al-Maftūnu | 068-006 ዕብደት በማንኛችሁ እንዳልለ፡፡ | بِأَيّيِكُمُ الْمَفْتُونُ |
'Inna Rabbaka Huwa 'A`lamu Biman Đalla `An Sabīlihi Wa Huwa 'A`lamu Bil-Muhtadīna | 068-007 ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ተመሪዎቹን ዐዋቂ ነው፡፡ | إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَنْ ضَلَّ عَنْ سَبِيلِهِ وَهُوَ أَعْلَمُ بِالْمُهْتَدِينَ |
Falā Tuţi`i Al-Mukadhdhibīna | 068-008 ለአስተባባዮችም አትታዝዙ፡፡ | فَلاَ تُطِعِ الْمُكَذِّبِينَ |
Wa Ddū Law Tud/hinu Fayud/hinūna | 068-009 ብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ፡፡ | وَدُّوا لَوْ تُدْهِنُ فَيُدْهِنُونَ |
Wa Lā Tuţi` Kulla Ĥallāfin Mahīnin | 068-010 ወራዳንም ሁሉ አትታዘዝ፡፡ | وَلاَ تُطِعْ كُلَّ حَلاَّفٍ مَهِينٍ |
Hammāzin Mashshā'in Binamīmin | 068-011 ሰውን አነዋሪንና በማሳበቅ ኼያጅን፡፡ | هَمَّازٍ مَشَّاءٍ بِنَمِيمٍ |
Mannā`in Lilkhayri Mu`tadin 'Athīmin | 068-012 ለበጎ ነገር በጣም ከልካይን፣ ወሰን አላፊን፣ ኃጢአተኛን፤ | مَنَّاعٍ لِلْخَيْرِ مُعْتَدٍ أَثِيمٍ |
`Utullin Ba`da Dhālika Zanīmin | 068-013 ልበ ደረቅን፣ ከዚህ በኋላ ዲቃላን (ሁሉ አትታዘዝ)፡፡ | عُتُلٍّ بَعْدَ ذَلِكَ زَنِيمٍ |
'An Kāna Dhā Mālin Wa Banīna | 068-014 የገንዘብና የልጆች ባለቤት በመኾኑ (ያስተባብላል)፡፡ | أَنْ كَانَ ذَا مَالٍ وَبَنِينَ |
'Idhā Tutlá `Alayhi 'Āyātunā Qāla 'Asāţīru Al-'Awwalīna | 068-015 በእርሱ ላይ አንቀጾቻችን በሚነበቡ ጊዜ آ«የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸውآ» ይላል፡፡ | إِذَا تُتْلَى عَلَيْهِ آيَاتُنَا قَالَ أَسَاطِيرُ الأَوَّلِينَ |
Sanasimuhu `Alá Al-Khurţūmi | 068-016 በአፍንጫው ላይ በእርግጥ (የሚነወርበት) ምልክት እናደርግበታለን፡፡ | سَنَسِمُهُ عَلَى الْخُرْطُومِ |
'Innā Balawnāhum Kamā Balawnā 'Aşĥāba Al-Jannati 'Idh 'Aqsamū Layaşrimunnahā Muşbiĥīna | 068-017 እኛ የአትክልቲቱን ባለቤቶቸ እንደ ሞከርን (የመካን ሰዎች) ሞከርናቸው፡፡ ማልደው (ፍሬዋን) ሊለቅሟት በማሉ ጊዜ፡፡ | إِنَّا بَلَوْنَاهُمْ كَمَا بَلَوْنَا أَصْحَابَ الْجَنَّةِ إِذْ أَقْسَمُوا لَيَصْرِمُنَّهَا مُصْبِحِينَ |
Wa Lā Yastathnūna | 068-018 (በመሓላቸው) አያስቀሩምም፡፡ | وَلاَ يَسْتَثْنُونَ |
Faţāfa `Alayhā Ţā'ifun Min Rabbika Wa Hum Nā'imūna | 068-019 እነርሱ የተኙ ኾነውም ሳሉ ከጌታህ የኾነ ዟሪ በእርሷ ላይ ዞረባት፡፡ | فَطَافَ عَلَيْهَا طَائِفٌ مِنْ رَبِّكَ وَهُمْ نَائِمُونَ |
Fa'aşbaĥat Kālşşarīmi | 068-020 እንደ ሌሊት ጨለማም ኾና አነጋች፤ (ከሰለች)፡፡ | فَأَصْبَحَتْ كَالصَّرِيمِ |
Fatanādaw Muşbiĥīna | 068-021 ያነጉም ኾነው ተጠራሩ፡፡ | فَتَنَادَوا مُصْبِحِينَ |
'Ani Aghdū `Alá Ĥarthikum 'In Kuntum Şārimīna | 068-022 آ«ቆራጮች እንደ ኾናችሁ በእርሻቸሁ ላይ ማልዱآ» በማለት፡፡ | أَنِ اغْدُوا عَلَى حَرْثِكُمْ إِنْ كُنتُمْ صَارِمِينَ |
Fānţalaqū Wa Hum Yatakhāfatūna | 068-023 እነርሱ የሚንሾካሾኩ ኾነው ኼዱም፡፡ | فَانطَلَقُوا وَهُمْ يَتَخَافَتُونَ |
'An Lā Yadkhulannahā Al-Yawma `Alaykum Miskīnun | 068-024 ዛሬ በእናንተ ላይ ድኻ እንዳይገባት በማለት፡፡ | أَنْ لاَ يَدْخُلَنَّهَا الْيَوْمَ عَلَيْكُمْ مِسْكِينٌ |
Waghadaw `Alá Ĥardin Qādirīna | 068-025 (ድኾችን) በመከልከልም ላይ (በሐሳባቸው) ቻዮች ኾነው ማለዱ፡፡ | وَغَدَوْا عَلَى حَرْدٍ قَادِرِينَ |
Falammā Ra'awhā Qālū 'Innā Lađāllūna | 068-026 (ተቃጥላ) ባዩዋትም ጊዜ آ«እኛ በእርግጥ ተሳሳቾች ነንآ» አሉ፡፡ | فَلَمَّا رَأَوْهَا قَالُوا إِنَّا لَضَالُّونَ |
Bal Naĥnu Maĥrūmūna | 068-027 آ«ይልቁንም እኛ የተከለከልን ነንآ» አሉ፡፡ | بَلْ نَحْنُ مَحْرُومُونَ |
Qāla 'Awsaţuhum 'Alam 'Aqul Lakum Lawlā Tusabbiĥūna | 068-028 ትክክለኛቸው آ«ለእናንተ አላህን ለምን አታጠሩም አላልኳችሁምን?آ» አላቸው፡፡ | قَالَ أَوْسَطُهُمْ أَلَمْ أَقُلْ لَكُمْ لَوْلاَ تُسَبِّحُونَ |
Qālū Subĥāna Rabbinā 'Innā Kunnā Žālimīna | 068-029 آ«ጌታችን ጥራት ይገባው፡፡ እኛ በዳዮች ነበርን፤آ» አሉ፡፡ | قَالُوا سُبْحَانَ رَبِّنَا إِنَّا كُنَّا ظَالِمِينَ |
Fa'aqbala Ba`đuhum `Alá Ba`đin Yatalāwamūna | 068-030 የሚወቃቀሱም ኾነው ከፊሎቻቸው በከፊሉ ላይ መጡ፡፡ | فَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَى بَعْضٍ يَتَلاَوَمُونَ |
Qālū Yā Waylanā 'Innā Kunnā Ţāghīna | 068-031 آ«ዋ ጥፋታችን! እኛ ድንበር አላፊዎች ነበርን፤آ» አሉ፡፡ | قَالُوا يَا وَيْلَنَا إِنَّا كُنَّا طَاغِينَ |
`Asá Rabbunā 'An Yubdilanā Khayrāan Minhā 'Innā 'Ilá Rabbinā Rāghibūna | 068-032 آ«ጌታችን ከእርሷ የተሻለን (አትክልት) ሊለውጠን ይከጀላል፡፡ እኛ ወደ ጌታችን ከጃዮች ነን፤آ» (አሉ)፡፡ | عَسَى رَبُّنَا أَنْ يُبْدِلَنَا خَيْراً مِنْهَا إِنَّا إِلَى رَبِّنَا رَاغِبُونَ |
Kadhālika Al-`Adhābu Wa La`adhābu Al-'Ākhirati 'Akbaru Law Kānū Ya`lamūna | 068-033 ቅጣቱ እንደዚሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት ታላቅ ነው፡፡ የሚያውቁት በኾኑ ኖሮ (በተጠነቀቁ ነበር)፡፡ | كَذَلِكَ الْعَذَابُ وَلَعَذَابُ الآخِرَةِ أَكْبَرُ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ |
'Inna Lilmuttaqīna `Inda Rabbihim Jannāti An-Na`īmi | 068-034 ለጥንቁቆቹ በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው፡፡ | إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ عِنْدَ رَبِّهِمْ جَنَّاتِ النَّعِيمِ |
'Afanaj`alu Al-Muslimīna Kālmujrimīna | 068-035 ሙስሊሞቹን እንደ ከሓዲዎች እናደርጋለን? | أَفَنَجْعَلُ الْمُسْلِمِينَ كَالْمُجْرِمِينَ |
Mā Lakum Kayfa Taĥkumūna | 068-036 ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ፡፡ | مَا لَكُمْ كَيْفَ تَحْكُمُونَ |
'Am Lakum Kitābun Fīhi Tadrusūna | 068-037 በእውነቱ ለእናንተ በእርሱ የምታጠኑበት መጽሐፍ አላችሁን? | أَمْ لَكُمْ كِتَابٌ فِيهِ تَدْرُسُونَ |
'Inna Lakum Fīhi Lamā Takhayyarūna | 068-038 በውስጡ ለእናንተ የምትመርጡት አላችሁ (የሚል) | إِنَّ لَكُمْ فِيهِ لَمَا تَخَيَّرُونَ |
'Am Lakum 'Aymānun `Alaynā Bālighatun 'Ilá Yawmi Al-Qiyāmati 'Inna Lakum Lamā Taĥkumūna | 068-039 ወይስ ለእናንተ የምትፈርዱት አላችሁ በማለት (ቃል ኪዳን የገባንላችሁ) እስከ ትንሣኤ ቀን ደራሽ የኾኑ መሓላዎች ለእናንተ በእኛ ላይ አሏችሁን? | أَمْ لَكُمْ أَيْمَانٌ عَلَيْنَا بَالِغَةٌ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ إِنَّ لَكُمْ لَمَا تَحْكُمُونَ |
Salhum 'Ayyuhum Bidhālika Za`īmun | 068-040 በዚህ ማንኛቸው ተያያዥ እንደ ኾነ ጠይቃቸው፡፡ | سَلْهُم أَيُّهُمْ بِذَلِكَ زَعِيمٌ |
'Am Lahum Shurakā'u Falya'tū Bishurakā'ihim 'In Kānū Şādiqīna | 068-041 ወይስ ለእነርሱ (በፍርዳቸው ተስማሚ) آ«ተጋሪዎችآ» አሏቸውን? እውነተኞችም እንደኾኑ آ«ተጋሪዎቻቸውንآ» ያምጡ፡፡ | أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ فَلْيَأْتُوا بِشُرَكَائِهِمْ إِنْ كَانُوا صَادِقِينَ |
Yawma Yukshafu `An Sāqin Wa Yud`awna 'Ilá As-Sujūdi Falā Yastaţī`ūna | 068-042 ባት የሚገለጥበትን (ከሓዲዎች) ወደ መስገድም የሚጥጠሩበትንና የማይችሉበት ቀን (አስታውስ)፡፡ | يَوْمَ يُكْشَفُ عَنْ سَاقٍ وَيُدْعَوْنَ إِلَى السُّجُودِ فَلاَ يَسْتَطِيعُونَ |
Khāshi`atan 'Abşāruhum Tarhaquhum Dhillatun Wa Qad Kānū Yud`awna 'Ilá As-Sujūdi Wa Hum Sālimūna | 068-043 ዓይኖቻቸው የፈሩ ውርደት የምትሸፍናቸው ሲኾኑ፤ (ወደ ስግደት የሚጠሩበትን)፤ እነርሱም (በምድረ ዓለም) ደህና ኾነው ሳሉ ወደ ስግደት በእርግጥ ይጠሩ ነበሩ፡፡ | خَاشِعَةً أَبْصَارُهُمْ تَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ وَقَدْ كَانُوا يُدْعَوْنَ إِلَى السُّجُودِ وَهُمْ سَالِمُونَ |
Fadharnī Wa Man Yukadhdhibu Bihadhā Al-Ĥadīthi Sanastadrijuhum Min Ĥaythu Lā Ya`lamūna | 068-044 በዚህም ንግግር ከሚያስተባብሉት ሰዎች ጋር ተዎኝ፡፡ (እነርሱን እኔ እበቃሃለሁ)፡፡ ከማያውቁት ስፍራ አዘናግተን እንይዛቸዋለን፡፡ | فَذَرْنِي وَمَنْ يُكَذِّبُ بِهَذَا الْحَدِيثِ سَنَسْتَدْرِجُهُمْ مِنْ حَيْثُ لاَ يَعْلَمُونَ |
Wa 'Umlī Lahum 'Inna Kaydī Matīnun | 068-045 እነርሱንም አዘገያለሁ፡፡ ዘዴዬ ብርቱ ነውና፡፡ | وَأُمْلِي لَهُمْ إِنَّ كَيْدِي مَتِينٌ |
'Am Tas'aluhum 'Ajrāan Fahum Min Maghramin Muthqalūna | 068-046 በእውነቱ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳ የተከበዱ ናቸውን? | أَمْ تَسْأَلُهُمْ أَجْراً فَهُمْ مِنْ مَغْرَمٍ مُثْقَلُونَ |
'Am `Indahumu Al-Ghaybu Fahum Yaktubūna | 068-047 ወይስ እነርሱ ዘንድ የሩቁ ምስጢር ዕውቀት አልለን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን? | أَمْ عِنْدَهُمُ الْغَيْبُ فَهُمْ يَكْتُبُونَ |
Fāşbir Liĥukmi Rabbika Wa Lā Takun Kaşāĥibi Al-Ĥūti 'Idh Nādá Wa Huwa Makžūmun | 068-048 ለጌታህም ፍርድ ታገሥ፤ (በመበሳጨትና ባለ መታገሥ) እንደ ዓሣው ባለቤትም (እንደ ዮናስ) አትኹን፡፡ እርሱ በጭንቀት የተመላ ኾኖ (ጌታውን) በተጣራ ጊዜ፡፡ | فَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ وَلاَ تَكُنْ كَصَاحِبِ الْحُوتِ إِذْ نَادَى وَهُوَ مَكْظُومٌ |
Lawlā 'An Tadārakahu Ni`matun Min Rabbihi Lanubidha Bil-`Arā'i Wa Huwa Madhmūmun | 068-049 ከጌታው የኾነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ በምድረ በዳ ተወቃሽ ኾኖ በተጣለ ነበር፡፡ | لَوْلاَ أَنْ تَدَارَكَهُ نِعْمَةٌ مِنْ رَبِّهِ لَنُبِذَ بِالْعَرَاءِ وَهُوَ مَذْمُومٌ |
Fājtabāhu Rabbuhu Faja`alahu Mina Aş-Şāliĥīna | 068-050 ጌታውም (በነቢይነት) መረጠው፡፡ ከደጋጎቹም አደረገው፡፡ | فَاجْتَبَاهُ رَبُّهُ فَجَعَلَهُ مِنَ الصَّالِحِينَ |
Wa 'In Yakādu Al-Ladhīna Kafarū Layuzliqūnaka Bi'abşārihim Lammā Sami`ū Adh-Dhikra Wa Yaqūlūna 'Innahu Lamajnūnun | 068-051 እነሆ እነዚያም የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቀርባሉ፡፡ آ«እርሱም በእርግጥ ዕብድ ነውآ» ይላሉ፡፡ | وَإِنْ يَكَادُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَيُزْلِقُونَكَ بِأَبْصَارِهِمْ لَمَّا سَمِعُوا الذِّكْرَ وَيَقُولُونَ إِنَّهُ لَمَجْنُونٌ |
Wa Mā Huwa 'Illā Dhikrun Lil`ālamīna | 068-052 ግን እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ | وَمَا هُوَ إِلاَّ ذِكْرٌ لِلْعَالَمِينَ |