67) Sūrat Al-Mulk

Printed format

67) سُورَة المُلك

Tabāraka Al-Ladhī Biyadihi Al-Mulku Wa Huwa `Alá Kulli Shay'in Qadīrun 067-001 ያ ንግሥና በእጁ የኾነው አምላክ ችሮታው በዛ፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ تَبَارَكَ ا‍لَّذِي بِيَدِهِ ا‍لْمُلْكُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْء‍ٍ قَد‍ِي‍ر‍ٌ
Al-Ladhī Khalaqa Al-Mawta Wa Al-Ĥayāata Liyabluwakum 'Ayyukum 'Aĥsanu `Amalāan Wa Huwa Al-`Azīzu Al-Ghafūru 067-002 ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡ ا‍لَّذِي خَلَقَ ا‍لْمَوْتَ وَا‍لْحَي‍‍َ‍ا‍ةَ لِيَ‍‍ب‍‍ْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلا‍ً وَهُوَ ا‍لْعَز‍ِي‍زُ ا‍لْغَف‍‍ُ‍و‍رُ
Al-Ladhī Khalaqa Sab`a Samāwātin Ţibāqāan Mā Tará Fī Khalqi Ar-Raĥmāni Min Tafāwutin Fārji`i Al-Başara Hal Tará Min Fuţūrin 067-003 ያ ሰባትን ሰማያት የተነባበሩ ኾነው የፈጠረ ነው፡፡ በአልረሕማን አፈጣጠር ውስጥ ምንም መዛነፍን አታይም፡፡ ዓይንህንም መልስ፡፡ آ«ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን?آ» ا‍لَّذِي خَلَقَ سَ‍‍ب‍‍ْعَ سَمَاو‍َا‍ت‍‍‍ٍ طِبَاقا‍ً مَا تَرَى فِي خَلْقِ ا‍لرَّحْمَنِ مِ‍‍ن‍ْ تَفَاوُت‍‍‍ٍ فَارْجِعِ ا‍لْبَصَرَ هَلْ تَرَى مِ‍‍ن‍ْ فُط‍‍ُ‍و‍ر‍ٍ
Thumma Arji`i Al-Başara Karratayni Yanqalib 'Ilayka Al-Başaru Khāsi'āan Wa Huwa Ĥasīrun 067-004 ከዚያም ብዙ ጊዜ ዓይንህን መላልስ፡፡ ዓይንህ ተዋርዶ እርሱም የደከመ ኾኖ ወዳንተ ይመለሳል፡፡ ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ ا‍رْجِعِ ا‍لْبَصَرَ كَرَّتَيْنِ يَ‍‍ن‍قَلِ‍‍ب‍ْ إِلَيْكَ ا‍لْبَصَرُ خَاسِئا‍ً وَهُوَ حَس‍‍ِ‍ي‍ر‍ٌ
Wa Laqad Zayyannā As-Samā'a Ad-Dunyā Bimaşābīĥa Wa Ja`alnāhā Rujūmāan Lilshshayāţīni Wa 'A`tadnā Lahum `Adhāba As-Sa`īri 067-005 ቅርቢቱን ሰማይም በእርግጥ በመብራቶች (በከዋክብት) አጌጥናት፡፡ ለሰይጣናትም መቀጥቀጫዎች አደረግናት፡፡ ለእነርሱም (ለሰይጣኖች) የእሳትን ቅጣት አዘጋጀን፡፡ وَلَقَ‍‍د‍ْ زَيَّ‍‍ن‍ّ‍‍َا ا‍لسَّم‍‍َ‍ا‍ءَ ا‍لدُّ‍‍ن‍‍ْيَا بِمَصَاب‍‍ِ‍ي‍حَ وَجَعَلْنَاهَا رُجُوما‍ً لِلشَّيَاط‍‍ِ‍ي‍نِ وَأَعْتَ‍‍د‍‍ْنَا لَهُمْ عَذ‍َا‍بَ ا‍لسَّع‍‍ِ‍ي‍رِ
Wa Lilladhīna Kafarū Birabbihim `Adhābu Jahannama Wa Bi'sa Al-Maşīru 067-006 ለእነዚያም በጌታቸው ለካዱት የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ መመለሻይቱም ከፋች! وَلِلَّذ‍ِي‍نَ كَفَرُوا‍ بِرَبِّهِمْ عَذ‍َا‍بُ جَهَ‍‍ن‍ّ‍‍َمَ وَبِئْسَ ا‍لْمَص‍‍ِ‍ي‍‍ر‍ُ
'Idhā 'Ulqū Fīhā Sami`ū Lahā Shahīqāan Wa Hiya Tafūru 067-007 በውስጧ በተጣሉ ጊዜ፤ እርሷ የምትፈላ ስትኾን ለእርሷ (እንደ አህያ) ማናፋትን ይሰማሉ፡፡ إِذَا أُلْقُو‍‍ا‍ فِيهَا سَمِعُو‍‍ا‍ لَهَا شَهِيقا‍ً وَهِيَ تَف‍‍ُ‍و‍رُ
Takādu Tamayyazu Mina Al-Ghayži Kullamā 'Ulqiya Fīhā Fawjun Sa'alahum Khazanatuhā 'Alam Ya'tikum Nadhīrun 067-008 ከቁጭትዋ የተነሳ ልትቆራረጥ ትቀርባለች፡፡ በውስጧ ጭፍሮች በተጣሉ ቁጥር ዘበኞችዋ آ«አስፈራሪ (ነቢይ) አልመጣችሁምን?آ» በማለት ይጠይቋቸዋል፡፡ تَك‍‍َ‍ا‍دُ تَمَيَّزُ مِنَ ا‍لْغَيْظِ كُلَّمَ‍‍ا‍ أُلْقِيَ فِيهَا فَوْج‍‍‍ٌ سَأَلَهُمْ خَزَنَتُهَ‍‍ا‍ أَلَمْ يَأْتِكُمْ نَذ‍ِي‍ر‍ٌ
Qālū Balá Qad Jā'anā Nadhīrun Fakadhdhabnā Wa Qulnā Mā Nazzala Al-Lahu Min Shay'in 'In 'Antum 'Illā Fī Đalālin Kabīrin 067-009 آ«አይደለም በእርግጥ አስፈራሪ መጥቶናል፡፡ አስተባበልንም፡፡ አላህም ምንንም አላወረደ እናንተ (አውርዷል ስትሉ) በትልቅ ስህተት ውስጥ እንጅ አይደላችሁም አልንآ» ይላሉ፡፡ قَالُو‍‍ا‍ بَلَى قَ‍‍د‍ْ ج‍‍َ‍ا‍ءَنَا نَذ‍ِي‍ر‍ٌ فَكَذَّ‍‍ب‍‍ْنَا وَقُلْنَا مَا نَزَّلَ ا‍للَّهُ مِ‍‍ن‍ْ شَيْء‍ٍ إِنْ أَ‍ن‍‍ْتُمْ إِلاَّ فِي ضَلاَل‍‍‍ٍ كَب‍‍ِ‍ي‍ر‍ٍ
Wa Qālū Law Kunnā Nasma`u 'Aw Na`qilu Mā Kunnā Fī 'Aşĥābi As-Sa`īri 067-010 آ«የምንሰማ ወይም የምናስብ በነበርንም ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልኾን ነበርآ» ይላሉ፡፡ وَقَالُو‍‍ا‍ لَوْ كُ‍‍ن‍ّ‍‍َا نَسْمَعُ أَوْ نَعْقِلُ مَا كُ‍‍ن‍ّ‍‍َا فِ‍‍ي‍ أَصْح‍‍َ‍ا‍بِ ا‍لسَّع‍‍ِ‍ي‍رِ
Fā`tarafū Bidhanbihim Fasuĥqāan Li'şĥābi As-Sa`īri 067-011 በኀጢኣታቸውም ያምናሉ ለእሳት ጓዶችም (ከእዝነት) መራቅ ተገባቸው፡፡ فَاعْتَرَفُو‍‍ا‍ بِذَ‍ن‍‍ْبِهِمْ فَسُحْقا‍ً لِأصْح‍‍َ‍ا‍بِ ا‍لسَّع‍‍ِ‍ي‍رِ
'Inna Al-Ladhīna Yakhshawna Rabbahum Bil-Ghaybi Lahum Maghfiratun Wa 'Ajrun Kabīrun 067-012 እነዚያ ጌታቸውን በሩቁ የሚፈሩ ለእነርሱ ምሕረትና ታላቅ ምንዳ አልላቸው፡፡ إِ‍نّ‍‍َ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُ‍‍م‍ْ بِ‍‍ا‍لْغَيْبِ لَهُ‍‍م‍ْ مَغْفِرَة‍‍‍ٌ وَأَ‍ج‍‍ْر‍ٌ كَب‍‍ِ‍ي‍ر‍ٌ
Wa 'Asirrū Qawlakum 'Aw Ajharū Bihi 'Innahu `Alīmun Bidhāti Aş-Şudūri 067-013 (ሰዎች ሆይ!) ቃላችሁንም መስጥሩ፡፡ ወይም በእርሱ ጩሁ፡፡ እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ وَأَسِرُّوا‍ قَوْلَكُمْ أَوْ ا‍ج‍‍ْهَرُوا‍ بِهِ إِ‍نّ‍‍َهُ عَل‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٌ بِذ‍َا‍تِ ا‍لصُّد‍ُو‍ر‍ِ
'Alā Ya`lamu Man Khalaqa Wa Huwa Al-Laţīfu Al-Khabīru 067-014 የፈጠረ አምላክ እርሱ ዕውቀት ረቂቁ፣ ውስጥ ዐዋቂው ሲኾን (ምስጢርን ሁሉ) አያውቅምን? أَلاَ يَعْلَمُ مَنْ خَلَقَ وَهُوَ ا‍للَّط‍‍ِ‍ي‍فُ ا‍لْخَب‍‍ِ‍ي‍‍ر‍ُ
Huwa Al-Ladhī Ja`ala Lakumu Al-'Arđa Dhalūlāanmshū Fī Manākibihā Wa Kulū Min Rizqihi Wa 'Ilayhi An-Nushūru 067-015 እርሱ ያ ምድርን ለእናንተ የተገራች ያደረገላችሁ ነው፡፡ በጋራዎችዋና በመንገዶችዋም ኺዱ፡፡፡ ከሲሳዩም ብሉ፡፡ (ኋላ) መመለሻውም ወደእርሱ ብቻ ነው፡፡ هُوَ ا‍لَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ا‍لأَرْضَ ذَلُولا‍ً فَامْشُو‍‍ا‍ فِي مَنَاكِبِهَا وَكُلُو‍‍ا‍ مِ‍‍ن‍ْ ‍ر‍‍ِزْقِهِ وَإِلَيْهِ ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍ُش‍‍ُ‍و‍رُ
'A'amintum Man As-Samā'i 'An Yakhsifa Bikumu Al-'Arđa Fa'idhā Hiya Tamūru 067-016 በሰማይ ውስጥ ያለን (ሰራዊት) በእናንተ ምድርን ቢደረባባችሁ ወዲያውም እርሷ የምታረገርግ ብትኾን ትተማመናላችሁን? (አትፈሩምን?) أَأَمِ‍‍ن‍تُ‍‍م‍ْ مَ‍‍ن‍ْ فِي ا‍لسَّم‍‍َ‍ا‍ءِ أَ‍ن‍ْ يَخْسِفَ بِكُمُ ا‍لأَرْضَ فَإِذَا هِيَ تَم‍‍ُ‍و‍رُ
'Am 'Amintum Man As-Samā'i 'An Yursila `Alaykum Ĥāşibāan Fasata`lamūna Kayfa Nadhīri 067-017 ወይም በሰማይ ውስጥ ያለን በእናንተ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ቢልክባችሁ ትተማመናላችሁን? (አትፈሩምን?) ማስጠንቀቄም እንዴት እንደኾነ ወደፊት ታውቃላችሁ፡፡ أَمْ أَمِ‍‍ن‍تُ‍‍م‍ْ مَ‍‍ن‍ْ فِي ا‍لسَّم‍‍َ‍ا‍ءِ أَ‍ن‍ْ يُرْسِلَ عَلَيْكُمْ حَاصِبا‍ً فَسَتَعْلَم‍‍ُ‍و‍نَ كَيْفَ نَذ‍ِي‍رِ
Wa Laqad Kadhdhaba Al-Ladhīna Min Qablihim Fakayfa Kāna Nakīri 067-018 እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት በእርግጥ አስተባበሉ፡፡ ጥላቻዬም እንዴት ነበር! وَلَقَ‍‍د‍ْ كَذَّبَ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ مِ‍‍ن‍ْ قَ‍‍ب‍‍ْلِهِمْ فَكَيْفَ ك‍‍َ‍ا‍نَ نَك‍‍ِ‍ي‍رِ
'Awalam Yaraw 'Ilá Aţ-Ţayri Fawqahum Şāffātin Wa Yaqbiđna Mā Yumsikuhunna 'Illā Ar-Raĥmānu 'Innahu Bikulli Shay'in Başīrun 067-019 ወደ አእዋፍ ከበላያቸው ክንፎቻቸውን ዘርግተው ተንሳፋፊዎች የሚሰበሰቡም ሲኾኑ አላዩምን? ከአልረሕማን በቀር (ባየር ላይ) የሚይዛቸው የለም፡፡ እርሱ በነገሩ ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا إِلَى ا‍لطَّيْ‍‍ر‍ِ فَوْقَهُمْ ص‍‍َ‍ا‍فّ‍‍َ‍ا‍ت‍‍‍ٍ وَيَ‍‍ق‍‍ْبِضْنَ مَا يُمْسِكُهُ‍‍ن‍ّ‍‍َ إِلاَّ ا‍لرَّحْمَنُ إِ‍نّ‍‍َهُ بِكُلِّ شَيْء‍ٍ بَص‍‍ِ‍ي‍ر‍ٌ
'Amman Hādhā Al-Ladhī Huwa Jundun Lakum Yanşurukum Min Dūni Ar-Raĥmāni 'Ini Al-Kāfirūna 'Illā Fī Ghurūrin 067-020 በእውነቱ ያ እርሱ ከአልረሕማን ሌላ የሚረዳችሁ ለእናንተ የኾነ ሰራዊት ማነው? ከሓዲዎች በመታለል ውስጥ እንጅ በሌላ ላይ አይደሉም፡፡ أَ‍مّ‍‍َنْ هَذَا ا‍لَّذِي هُوَ جُ‍‍ن‍د‍ٌ لَكُمْ يَ‍‍ن‍صُرُكُ‍‍م‍ْ مِ‍‍ن‍ْ د‍ُو‍نِ ا‍لرَّحْمَنِ إِنِ ا‍لْكَافِر‍ُو‍نَ إِلاَّ فِي غُر‍ُو‍ر‍ٍ
'Amman Hādhā Al-Ladhī Yarzuqukum 'In 'Amsaka Rizqahu Bal Lajjū Fī `Utūwin Wa Nufūrin 067-021 ወይም ሲሳዩን ቢይዝባችሁ ያ ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው? በእውነቱ እነርሱ በሞገድና በመደንበር ውስጥ ችክ አሉ፡፡ أَ‍مّ‍‍َنْ هَذَا ا‍لَّذِي يَرْزُقُكُمْ إِنْ أَمْسَكَ ‍ر‍‍ِزْقَهُ بَ‍‍ل‍ْ لَجُّو‍‍ا‍ فِي عُتُوّ‍ٍ وَنُف‍‍ُ‍و‍ر‍ٍ
'Afaman Yamshī Mukibbāan `Alá Wajhihi 'Ahdá 'Amman Yamshī Sawīyāan `Alá Şirāţin Mustaqīmin 067-022 በፊቱ ላይ ተደፍቶ የሚኼድ ሰው ይበልጥ የቀና ነውን? ወይስ በቀጥተኛ መንገድ ላይ ተስተካክሎ የሚኼድ? أَفَمَ‍‍ن‍ْ يَمْشِي مُكِبّاً عَلَى وَج‍‍ْهِهِ أَهْدَى أَ‍مّ‍‍َ‍‍ن‍ْ يَمْشِي سَوِيّاً عَلَى صِر‍َا‍ط‍‍‍ٍ مُسْتَق‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٍ
Qul Huwa Al-Ladhī 'Ansha'akum Wa Ja`ala Lakumu As-Sam`a Wa Al-'Abşāra Wa Al-'Af'idata Qalīlāan Mā Tashkurūna 067-023 آ«እርሱ ያ የፈጠራችሁ ለእናንተም መስሚያና ማያዎችን፣ ልቦችንም ያደረገላችሁ ነው፡፡ ጥቂትንም አታመስግኑምآ» በላቸው፡፡ قُلْ هُوَ ا‍لَّذِي أَن‍شَأَكُمْ وَجَعَلَ لَكُمُ ا‍لسَّمْعَ وَا‍لأَ‍ب‍‍ْص‍‍َ‍ا‍رَ وَا‍لأَفْئِدَةَ قَلِيلا‍ً مَا تَشْكُر‍ُو‍نَ
Qul Huwa Al-Ladhī Dhara'akum Al-'Arđi Wa 'Ilayhi Tuĥsharūna 067-024 آ«እርሱ ያ በምድር ላይ የበተናቸሁ ነው፡፡ ወደእርሱም ትሰበሰባላችሁآ» በላቸው፡፡ قُلْ هُوَ ا‍لَّذِي ذَرَأَكُمْ فِي ا‍لأَرْضِ وَإِلَيْهِ تُحْشَر‍ُو‍نَ
Wa Yaqūlūna Matá Hādhā Al-Wa`du 'In Kuntum Şādiqīna 067-025 آ«እውነተኞችም እንደኾናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?آ» ይላሉ፡፡ وَيَقُول‍‍ُ‍و‍نَ مَتَى هَذَا ا‍لْوَعْدُ إِ‍ن‍ْ كُ‍‍ن‍تُمْ صَادِق‍‍ِ‍ي‍نَ
Qul 'Innamā Al-`Ilmu `Inda Al-Lahi Wa 'Innamā 'Anā Nadhīrun Mubīnun 067-026 آ«ዕውቀቱ አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እኔ ግልጽ አስፈራሪ እንጅ ሌላ አይደለሁምآ» በላቸው፡፡ قُلْ إِ‍نّ‍‍َمَا ا‍لْعِلْمُ عِ‍‍ن‍‍ْدَ ا‍للَّهِ وَإِ‍نّ‍‍َمَ‍‍ا‍ أَنَا نَذ‍ِي‍ر‍ٌ مُب‍‍ِ‍ي‍ن‍‍‍ٌ
Falammā Ra'awhu Zulfatan Sī'at Wujūhu Al-Ladhīna Kafarū Wa Qīla Hādhā Al-Ladhī Kuntum Bihi Tadda`ūna 067-027 (ቅጣቱን) ቅርብ ኾኖ ባዩትም ጊዜ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ፊቶች ይክከፋሉ፡፡ آ«ይህ ያ በእርሱ ትከራከሩበት የነበራችሁት ነውآ» ይባላሉም፡፡ فَلَ‍‍م‍ّ‍‍َا رَأَوْهُ زُلْفَة‍‍‍ً س‍‍ِ‍ي‍ئَتْ وُج‍‍ُ‍و‍هُ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ كَفَرُوا‍ وَق‍‍ِ‍ي‍لَ هَذَا ا‍لَّذِي كُ‍‍ن‍تُ‍‍م‍ْ بِهِ تَدَّع‍‍ُ‍و‍نَ
Qul 'Ara'aytum 'In 'Ahlakaniya Al-Lahu Wa Man Ma`ī 'Aw Raĥimanā Faman Yujīru Al-Kāfirīna Min `Adhābin 'Alīmin 067-028 آ«አያችሁን? አላህ ቢገድለኝ ከእኔ ጋር ያሉትንም (እንደዚሁ) ወይም (በማቆየት) ቢያዝንልን ከሓዲዎችን ከአሳማሚ ቅጣት የሚያድን ማን ነው?آ» በላቸው፡፡ قُلْ أَرَأَيْتُمْ إِنْ أَهْلَكَنِيَ ا‍للَّهُ وَمَ‍‍ن‍ْ مَعِ‍‍ي‍ أَوْ رَحِمَنَا فَمَ‍‍ن‍ْ يُج‍‍ِ‍ي‍‍ر‍ُ ا‍لْكَافِ‍‍ر‍‍ِي‍نَ مِنْ عَذ‍َا‍بٍ أَل‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٍ
Qul Huwa Ar-Raĥmānu 'Āmannā Bihi Wa `Alayhi Tawakkalnā Fasata`lamūna Man Huwa Fī Đalālin Mubīnin 067-029 آ«እርሱ (እመኑበት የምላችሁ) አልረሕማን ነው፡፡ (እኛ) በእርሱ አመንን፡፡ በርሱም ላይ ተጠጋን፡፡ ወደ ፊትም በግልጽ መሳሳት ውስጥ የኾነው እርሱ ማን አንደ ኾነ በእርግጥ ታውቃላችሁآ» በላቸው፡፡ قُلْ هُوَ ا‍لرَّحْمَنُ آمَ‍‍ن‍ّ‍‍َا بِهِ وَعَلَيْهِ تَوَكَّلْنَا فَسَتَعْلَم‍‍ُ‍و‍نَ مَنْ هُوَ فِي ضَلاَل‍‍‍ٍ مُب‍‍ِ‍ي‍ن‍‍‍ٍ
Qul 'Ara'aytum 'In 'Aşbaĥa Mā'uukum Ghawrāan Faman Ya'tīkum Bimā'in Ma`īnin 067-030 آ«አያችሁን? ውሃችሁ ሠራጊ ቢኾን ፈሳሺን ውሃ የሚያመጣላቸሁ ማን ነው?آ» በላቸው፡፡ (አላህ የዓለማት ጌታ ያመጣዋል)፡፡ قُلْ أَرَأَيْتُمْ إِنْ أَصْبَحَ م‍‍َ‍ا‍ؤُكُمْ غَوْرا‍ً فَمَ‍‍ن‍ْ يَأْتِيكُ‍‍م‍ْ بِم‍‍َ‍ا‍ء‍ٍ مَع‍‍ِ‍ي‍ن‍‍‍ٍ
Next Sūrah