62) Sūrat Al-Jum`ah

Printed format

62) سُورَة الجُمعَه

Yusabbiĥu Lillahi Mā Fī As-Samāwāti Wa Mā Fī Al-'Arđi Al-Maliki Al-Quddūsi Al-`Azīzi Al-Ĥakīmi 062-001 በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ ለአላህ ንጉሥ፣ ቅዱስ፣ አሸናፊ፣ ጥበበኛ ለኾነው ያሞግሳል፡፡ يُسَبِّحُ لِلَّهِ مَا فِي ا‍لسَّمَاو‍َا‍تِ وَمَا فِي ا‍لأَرْضِ ا‍لْمَلِكِ ا‍لْقُدّ‍ُو‍سِ ا‍لْعَز‍ِي‍زِ ا‍لْحَك‍‍ِ‍ي‍مِ
Huwa Al-Ladhī Ba`atha Fī Al-'Ummīyīna Rasūlāan Minhum Yatlū `Alayhim 'Āyātihi Wa Yuzakkīhim Wa Yu`allimuhumu Al-Kitāba Wa Al-Ĥikmata Wa 'In Kānū Min Qablu Lafī Đalālin Mubīnin 062-002 እርሱ ያ በመሃይሞቹ ውስጥ አንቀጾቹን (ቁርኣንን) በእነርሱ ላይ የሚያነብላቸው፣ (ከማጋራት) የሚያጠራቸውም፣ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የኾነን መልክተኛ (ሙሐመድን) ከእነርሱው ውስጥ የላከ ነው፡፡ እነርሱም ከእርሱ በፊት በግልጽ ስሕተት ውስጥ ነበሩ፡፡ هُوَ ا‍لَّذِي بَعَثَ فِي ا‍لأُ‍مّ‍‍ِيّ‍‍ِ‍ي‍نَ رَسُولا‍ً مِنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِهِ وَيُزَكِّيهِمْ وَيُعَلِّمُهُمُ ا‍لْكِت‍‍َ‍ا‍بَ وَا‍لْحِكْمَةَ وَإِ‍ن‍ْ كَانُو‍‍ا‍ مِ‍‍ن‍ْ قَ‍‍ب‍‍ْلُ لَفِي ضَلاَل‍<
Wa 'Ākharīna Minhum Lammā Yalĥaqū Bihim Wa Huwa Al-`Azīzu Al-Ĥakīmu 062-003 ከነሱም ሌሎች ገና ያልተጠጉዋቸው በኾኑት ላይ (የላከው ነው)፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ وَآخَ‍‍ر‍‍ِي‍نَ مِنْهُمْ لَ‍‍م‍ّ‍‍َا يَلْحَقُو‍‍ا‍ بِهِمْ وَهُوَ ا‍لْعَز‍ِي‍زُ ا‍لْحَك‍‍ِ‍ي‍مُ
Dhālika Fađlu Al-Lahi Yu'utīhi Man Yashā'u Wa Allāhu Dhū Al-Fađli Al-`Ažīmi 062-004 ይህ የአላህ ችሮታ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ ذَلِكَ فَضْلُ ا‍للَّهِ يُؤْت‍‍ِ‍ي‍هِ مَ‍‍ن‍ْ يَش‍‍َ‍ا‍ءُ وَا‍للَّهُ ذُو ا‍لْفَضْلِ ا‍لْعَظ‍‍ِ‍ي‍مِ
Mathalu Al-Ladhīna Ĥummilū At-Tawrāata Thumma Lam Yaĥmilūhā Kamathali Al-Ĥimāri Yaĥmilu 'Asfārāan Bi'sa Mathalu Al-Qawmi Al-Ladhīna Kadhdhabū Bi'āyāti Al-Lahi Wa Allāhu Lā Yahdī Al-Qawma Až-Žālimīna 062-005 የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያም ያልተሸከሟት (ያልሠሩባት) ሰዎች ምሳሌ መጽሐፎችን እንደሚሸከም አህያ ብጤ ነው፡፡ የእነዚያ በአላህ አንቀጾች ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ከፋ፡፡ አላህም በዳዮችን ሕዝቦች አይመራም፡፡ مَثَلُ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ حُ‍‍م‍ّ‍‍ِلُو‍‍ا‍ ا‍لتَّوْر‍َا‍ةَ ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ لَمْ يَحْمِلُوهَا كَمَثَلِ ا‍لْحِم‍‍َ‍ا‍ر‍ِ يَحْمِلُ أَسْفَارا‍ً بِئْسَ مَثَلُ ا‍لْقَوْمِ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ كَذَّبُو‍‍ا‍ بِآي&zwj
Qul Yā 'Ayyuhā Al-Ladhīna Hādū 'In Za`amtum 'Annakum 'Awliyā 'U Lillahi Min Dūni An-Nāsi Fatamannaw Al-Mawta 'In Kuntum Şādiqīna 062-006 آ«እናንተ አይሁዳውያን የኾናችሁ ሆይ! ከሰው ሁሉ በስተቀር እናንተ ብቻ ለአላህ ወዳጆች ነን ብትሉ እውነተኞች እንደኾናችሁ ሞትን ተመኙآ» በላቸው፡፡ قُلْ ي‍‍َ‍ا‍أَيُّهَا ا‍لَّذ‍ِي‍نَ هَادُو‍ا‍ إِ‍ن‍ْ زَعَمْتُمْ أَ‍نّ‍‍َكُمْ أَوْلِي‍‍َ‍ا‍ءُ لِلَّهِ مِ‍‍ن‍ْ د‍ُو‍نِ ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َ‍ا‍سِ فَتَمَ‍‍ن‍ّ‍‍َوْا ا‍لْمَوْتَ إِ‍ن‍ْ كُ‍‍ن‍تُمْ صَادِق‍‍ِ‍ي‍نَ
Wa Lā Yatamannawnahu 'Abadāan Bimā Qaddamat 'Aydīhim Wa Allāhu `Alīmun Biž-Žālimīna 062-007 እጆቻቸውም ባስቀደሙት ኃጢአት ምክንያት በፍጹም አይመኙትም፡፡ አላህም በዳዮቹን ዐዋቂ ነው፡፡ وَلاَ يَتَمَ‍‍ن‍ّ‍‍َوْنَهُ أَبَدا‍ً بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيهِمْ وَا‍للَّهُ عَل‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٌ بِ‍‍ا‍لظَّالِم‍‍ِ‍ي‍نَ
Qul 'Inna Al-Mawta Al-Ladhī Tafirrūna Minhu Fa'innahu Mulāqīkum Thumma Turaddūna 'Ilá `Ālimi Al-Ghaybi Wa Ash-Shahādati Fayunabbi'ukum Bimā Kuntum Ta`malūna 062-008 آ«ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት እርሱ በእርግጥ አግኛችሁ ነው፡፡ ከዚያም ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ወደ ኾነው ጌታ ትመለሳላችሁ፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋልآ» በላቸው፡፡ قُلْ إِ‍نّ‍‍َ ا‍لْمَوْتَ ا‍لَّذِي تَفِرّ‍ُو‍نَ مِنْهُ فَإِ‍نّ‍‍َهُ مُلاَقِيكُمْ ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ تُرَدّ‍ُو‍نَ إِلَى عَالِمِ ا‍لْغَيْبِ وَا‍لشَّهَادَةِ فَيُنَبِّئُكُ‍‍م‍ْ بِمَا كُ‍‍ن‍تُمْ تَعْمَل‍‍ُ‍و‍نَ
Yā 'Ayyuhā Al-Ladhīna 'Āmanū 'Idhā Nūdī Lilşşalāati Min Yawmi Al-Jumu`ati Fās`aw 'Ilá Dhikri Al-Lahi Wa Dharū Al-Bay`a Dhālikum Khayrun Lakum 'In Kuntum Ta`lamūna 062-009 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ፡፡ ي‍َا‍أَيُّهَا ا‍لَّذ‍ِي‍نَ آمَنُ‍‍و‍‍ا‍ إِذَا نُودِي لِلصَّلاَةِ مِ‍‍ن‍ْ يَوْمِ ا‍لْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَى ذِكْ‍‍ر‍ِ ا‍للَّهِ وَذَرُوا‍ ا‍لْبَيْعَ ذَلِكُمْ خَيْر‍ٌ لَكُمْ إِ‍ن‍ْ كُ‍‍ن‍تُمْ تَعْلَم‍‍ُ‍و‍نَ
Fa'idhā Quđiyati Aş-Şalāatu Fāntashirū Fī Al-'Arđi Wa Abtaghū Min Fađli Al-Lahi Wa Adhkurū Al-Laha Kathīrāan La`allakum Tufliĥūna 062-010 ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ፡፡ ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ فَإِذَا قُضِيَتِ ا‍لصَّلاَةُ فَان‍تَشِرُوا‍ فِي ا‍لأَرْضِ وَا‍ب‍‍ْتَغُو‍‍ا‍ مِ‍‍ن‍ْ فَضْلِ ا‍للَّهِ وَا‍ذْكُرُوا‍ ا‍للَّهَ كَثِيرا‍ً لَعَلَّكُمْ تُفْلِح‍‍ُ‍و‍نَ
Wa 'Idhā Ra'aw Tijāratan 'Aw Lahwan Anfađđū 'Ilayhā Wa Tarakūka Qā'imāan Qul Mā `Inda Al-Lahi Khayrun Mina Al-Lahwi Wa Mina At-Tijārati Wa Allāhu Khayru Ar-Rāziqīna 062-011 ንግድን ወይም ዛዛታን ባዩ ጊዜም ቆመህ የተዉህ ሲኾኑ ወደእርሷ ይበተናሉ፡፡ አላህ ዘንድ ያለው ዋጋ ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው፡፡ آ«አላህም ከሰጪዎቹ ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን ሰጭ ነውآ» በላቸው፡፡ وَإِذَا رَأَوْا تِجَارَةً أَوْ لَهْوا‍ً ا‍ن‍فَضُّ‍‍و‍‍ا‍ إِلَيْهَا وَتَرَك‍‍ُ‍و‍كَ ق‍‍َ‍ا‍ئِما‍ً قُلْ مَا عِ‍‍ن‍‍ْدَ ا‍للَّهِ خَيْر‍ٌ مِنَ ا‍للَّهْوِ وَمِنَ ا‍لتِّجَارَةِ وَا‍للَّهُ خَيْرُ ا‍لرَّازِق‍‍ِ‍ي‍نَ
Next Sūrah