54) Sūrat Al-Qamar

Printed format

54) سُورَة القَمَر

Aqtarabati As-Sā`atu Wa Anshaqqa Al-Qamaru 054-001 ሰዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፡፡ ا‍ق‍‍ْتَرَبَتِ ا‍لسَّاعَةُ وَا‍ن‍‍ْشَقَّ ا‍لْقَمَرُ
Wa 'In Yaraw 'Āyatan Yu`riđū Wa Yaqūlū Siĥrun Mustamirrun 054-002 ተዓምርንም ቢያዩ (ከእምነት) ይዞራሉ፡፡ (ይህ) آ«ዘውታሪ ድግምት ነውምآ» ይላሉ፡፡ وَإِ‍ن‍ْ يَرَوْا آيَة‍‍‍ً يُعْ‍‍ر‍‍ِضُو‍‍ا‍ وَيَقُولُو‍‍ا‍ سِحْر‍ٌ مُسْتَمِرّ‍ٌ
Wa Kadhdhabū Wa Attaba`ū 'Ahwā'ahum Wa Kullu 'Amrin Mustaqirrun 054-003 አስተባበሉም፡፡ ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ፡፡ ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው)፤ ረጊ ነው፡፡ وَكَذَّبُو‍‍ا‍ وَا‍تَّبَعُ‍‍و‍‍ا‍ أَهْو‍َا‍ءَهُمْ وَكُلُّ أَمْر‍ٍ مُسْتَقِرّ‍ٌ
Wa Laqad Jā'ahum Mina Al-'Anbā'i Mā Fīhi Muzdajarun 054-004 ከዜናዎችም በእርሱ ውስጥ መገሰጥ ያለበት ነገር በእርግጥ መጣላቸው፡፡ وَلَقَ‍‍د‍ْ ج‍‍َ‍ا‍ءَهُ‍‍م‍ْ مِنَ ا‍لأَ‍ن‍‍ْب‍‍َ‍ا‍ءِ مَا ف‍‍ِ‍ي‍هِ مُزْدَجَر‍ٌ
Ĥikmatun Bālighatun Famā Tughni An-Nudhuru 054-005 ሙሉ የኾነች ጥበብ (መጣቻቸው) ግን አስፈራሪዎቹ አያብቃቁም፡፡ حِكْمَة‍‍‍ٌ بَالِغَة‍‍‍ٌ فَمَا تُغْنِ ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍ُذُرُ
Fatawalla `Anhum Yawma Yad`u Ad-Dā`i 'Ilá Shay'in Nukurin 054-006 ከነርሱም ዙር፡፡ ጠሪው (መልአክ) ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ فَتَوَلَّ عَنْهُمْ يَوْمَ يَ‍‍د‍‍ْعُ ا‍لدّ‍َا‍عِ إِلَى شَيْء‍ٍ نُكُر‍ٍ
Khushsha`āan 'Abşāruhum Yakhrujūna Mina Al-'Ajthi Ka'annahum Jarādun Muntashirun 054-007 ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ኾነው፤ ፍጹም የተበተነ አንበጣ መስለው ከመቃብሮቹ ይወጣሉ፡፡ خُشَّعاً أَ‍ب‍‍ْصَارُهُمْ يَخْرُج‍‍ُ‍و‍نَ مِنَ ا‍لأَ‍ج‍‍ْد‍َا‍ثِ كَأَ‍نّ‍‍َهُمْ جَر‍َا‍د‍ٌ مُ‍‍ن‍تَشِر‍ٌ
Muhţi`īna 'Ilá Ad-Dā`i Yaqūlu Al-Kāfirūna Hādhā Yawmun `Asirun 054-008 ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎች ቸኳዮች ኾነው (ይወጣሉ)፡፡ ከሓዲዎቹ (ያን ጊዜ ምን ይላሉ?) آ«ይህ ብርቱ ቀን ነውآ» ይላሉ፡፡ مُهْطِع‍‍ِ‍ي‍نَ إِلَى ا‍لدّ‍َا‍عِ يَق‍‍ُ‍و‍لُ ا‍لْكَافِر‍ُو‍نَ هَذَا يَوْمٌ عَسِر‍ٌ
Kadhdhabat Qablahum Qawmu Nūĥin Fakadhdhabū `Abdanā Wa Qālū Majnūnun Wa Azdujira 054-009 ከእነርሱ በፊት የኑሕ ነገድ አስተባበለች፡፡ ባሪያችንንም (ኑሕን) አስተባበሉ፡፡ آ«ዕብድ ነውምآ» አሉ፡፡ ተገላመጠም፡፡ كَذَّبَتْ قَ‍‍ب‍‍ْلَهُمْ قَوْمُ ن‍‍ُ‍و‍ح‍‍‍ٍ فَكَذَّبُو‍‍ا‍ عَ‍‍ب‍‍ْدَنَا وَقَالُو‍‍ا‍ مَ‍‍ج‍‍ْن‍‍ُ‍و‍ن‍‍‍ٌ وَا‍زْدُجِ‍‍ر‍َ
Fada`ā Rabbahu 'Annī Maghlūbunntaşir 054-010 ጌታውንም آ«እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝآ» ሲል ጠራ፡፡ فَدَعَا رَبَّهُ أَ‍نّ‍‍ِي مَغْل‍‍ُ‍و‍ب‍‍‍ٌ فَا‍ن‍‍ْتَصِرْ
Fafataĥnā 'Abwāba As-Samā'i Bimā'in Munhamirin 054-011 ወዲያውም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን፡፡ فَفَتَحْنَ‍‍ا‍ أَ‍ب‍‍ْو‍َا‍بَ ا‍لسَّم‍‍َ‍ا‍ءِ بِم‍‍َ‍ا‍ء‍ٍ مُنْهَمِر‍ٍ
Wa Fajjarnā Al-'Arđa `Uyūnāan Fāltaqá Al-Mā'u `Alá 'Amrin Qad Qudira 054-012 የምድርንም ምንጮች አፈነዳን፡፡ ውሃውም (የሰማዩና የምድሩ) በእርግጥ በተወሰነ ኹነታ ላይ ተገናኘ፡፡ وَفَجَّرْنَا ا‍لأَرْضَ عُيُونا‍ً فَا‍ل‍‍ْتَقَى ا‍لْم‍‍َ‍ا‍ءُ عَلَى أَمْر‍ٍ قَ‍‍د‍ْ قُدِ‍ر‍َ
Wa Ĥamalnāhu `Alá Dhāti 'Alwāĥin Wa Dusurin 054-013 ባለ ሳንቃዎችና ባለሚስማሮች በኾነችም ታንኳ ላይ ጫንነው፡፡ وَحَمَلْن‍‍َ‍ا‍هُ عَلَى ذ‍َا‍تِ أَلْو‍َا‍ح‍‍‍ٍ وَدُسُر‍ٍ
Tajrī Bi'a`yuninā Jazā'an Liman Kāna Kufira 054-014 በጥበቃችን ስር ኾና ትንሻለላለች፡፡ ተክዶ ለነበረው ሰው ምንዳ (ይህንን ሠራን)፡፡ تَ‍‍ج‍‍ْ‍‍ر‍‍ِي بِأَعْيُنِنَا جَز‍َا‍ء‍ً لِمَ‍‍ن‍ْ ك‍‍َ‍ا‍نَ كُفِ‍‍ر‍َ
Wa Laqad Taraknāhā 'Āyatan Fahal Min Muddakirin 054-015 ተዓምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት፡፡ ከተገሳጭም አልለን? وَلَقَ‍‍د‍ْ تَرَكْنَاهَ‍‍ا آيَة‍‍‍ً فَهَلْ مِ‍‍ن‍ْ مُدَّكِر‍ٍ
Fakayfa Kāna `Adhābī Wa Nudhuri 054-016 ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ? فَكَيْفَ ك‍‍َ‍ا‍نَ عَذَابِي وَنُذُ‍ر‍ِ
Wa Laqad Yassarnā Al-Qur'āna Lildhdhikri Fahal Min Muddakirin 054-017 ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገንዛቢም አልለን? وَلَقَ‍‍د‍ْ يَسَّرْنَا ا‍لْقُرْآنَ لِلذِّكْ‍‍ر‍ِ فَهَلْ مِ‍‍ن‍ْ مُدَّكِر‍ٍ
Kadhdhabat `Ādun Fakayfa Kāna `Adhābī Wa Nudhuri 054-018 ዓድ አስተባበለች፡፡ ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ! كَذَّبَتْ ع‍‍َ‍ا‍د‍ٌ فَكَيْفَ ك‍‍َ‍ا‍نَ عَذَابِي وَنُذُ‍ر‍ِ
'Innā 'Arsalnā `Alayhim Rīĥāan Şarşarāan Fī Yawmi Naĥsin Mustamirrin 054-019 እኛ በእነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በኾነ ቀን በኀይል የምትንሻሻ ነፋስን ላክንባቸው፡፡ إِ‍نّ‍‍َ‍‍ا‍ أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ ‍ر‍‍ِيحا‍ً صَرْصَرا‍ً فِي يَوْمِ نَحْس‍‍‍ٍ مُسْتَمِرّ‍ٍ
Tanzi`u An-Nāsa Ka'annahum 'A`jāzu Nakhlin Munqa`irin 054-020 ሰዎቹን ልክ ከሥሮቻቸው የተጎለሰሱ የዘንባባ ግንዶች መስለው (ከተደበቁበት) ትነቅላቸዋለች፡፡ تَ‍‍ن‍زِعُ ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َ‍ا‍سَ كَأَ‍نّ‍‍َهُمْ أَعْج‍‍َ‍ا‍زُ نَخْل‍‍‍ٍ مُ‍‍ن‍‍ْقَعِر‍ٍ
Fakayfa Kāna `Adhābī Wa Nudhuri 054-021 ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ? فَكَيْفَ ك‍‍َ‍ا‍نَ عَذَابِي وَنُذُ‍ر‍ِ
Wa Laqad Yassarnā Al-Qur'āna Lildhdhikri Fahal Min Muddakirin 054-022 ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን? وَلَقَ‍‍د‍ْ يَسَّرْنَا ا‍لْقُرْآنَ لِلذِّكْ‍‍ر‍ِ فَهَلْ مِ‍‍ن‍ْ مُدَّكِر‍ٍ
Kadhdhabat Thamūdu Bin-Nudhuri 054-023 ሰሙድ በአስፈራሪዎቹ አስተባበለች፡፡ كَذَّبَتْ ثَم‍‍ُ‍و‍دُ بِ‍‍ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍ُذُ‍ر‍ِ
Faqālū 'Abasharāan Minnā Wāĥidāan Nattabi`uhu 'Innā 'Idhāan Lafī Đalālin Wa Su`urin 054-024 آ«ከእኛ የኾነን አንድን ሰው እንከተለዋለን? እኛ ያን ጊዜ በስህተትና በዕብደት ውስጥ ነንآ» አሉ፡፡ فَقَالُ‍‍و‍‍ا‍ أَبَشَرا‍ً مِ‍‍ن‍ّ‍‍َا وَا‍حِدا‍ً نَتَّبِعُهُ إِ‍نّ‍‍َ‍‍ا إِذا‍ً لَفِي ضَلاَل‍‍‍ٍ وَسُعُر‍ٍ
'A'uulqiya Adh-Dhikru `Alayhi Min Bayninā Bal Huwa Kadhdhābun 'Ashirun 054-025 آ«ከኛ መካከል በእርሱ ላይ (ብቻ) ማስገንዘቢያ (ራእይ) ተጣለለትን? አይደለም እርሱ ውሸታም ኩሩ ነውآ» (አሉ)፡፡ أَؤُلْقِيَ ا‍لذِّكْرُ عَلَيْهِ مِ‍‍ن‍ْ بَيْنِنَا بَلْ هُوَ كَذّ‍َا‍بٌ أَشِر‍ٌ
Saya`lamūna Ghadāan Mani Al-Kadhdhābu Al-'Ashiru 054-026 ውሸታሙ ኩሩው ማን እንደኾነ ነገ በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ سَيَعْلَم‍‍ُ‍و‍نَ غَدا‍ً مَنِ ا‍لْكَذّ‍َا‍بُ ا‍لأَشِ‍‍ر‍ُ
'Innā Mursilū An-Nāqati Fitnatan Lahum Fārtaqibhum Wa Aşţabir 054-027 እኛ ሴት ግመልን ለእነርሱ መፈተኛ ትኾን ዘንድ ላኪዎች ነን፡፡ ተጠባበቃቸውም፡፡ ታገስም፡፡ إِ‍نّ‍‍َا مُرْسِلُو ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َاقَةِ فِتْنَة‍‍‍ً لَهُمْ فَارْتَقِ‍‍ب‍‍ْهُمْ وَا‍صْطَبِرْ
Wa Nabbi'hum 'Anna Al-Mā'a Qismatun Baynahum Kullu Shirbin Muĥtađarun 054-028 ውሃውንም በመካከላቸው የተከፈለ መኾኑን ንገራቸው፡፡ ከውሃ የኾነ ፋንታ ሁሉ (ተረኞቹ) የሚጣዱት ነው፡፡ وَنَبِّئْهُمْ أَ‍نّ‍‍َ ا‍لْم‍‍َ‍ا‍ءَ قِسْمَة‍‍‍ٌ بَيْنَهُمْ كُلُّ شِرْب‍‍‍ٍ مُحْتَضَر‍ٌ
Fanādaw Şāĥibahum Fata`āţá Fa`aqara 054-029 ጓደኛቸውንም ጠሩ፡፡ ወዲያውም (ሰይፍን) ተቀበለ፡፡ ወጋትም፡፡ فَنَادَوْا صَاحِبَهُمْ فَتَعَاطَى فَعَقَرَ
Fakayfa Kāna `Adhābī Wa Nudhuri 054-030 ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ? فَكَيْفَ ك‍‍َ‍ا‍نَ عَذَابِي وَنُذُ‍ر‍ِ
'Innā 'Arsalnā `Alayhim Şayĥatan Wāĥidatan Fakānū Kahashīmi Al-Muĥtažiri 054-031 እኛ በእነርሱ ላይ አንዲትን ጩኸት ላክንባቸው፡፡ ወዲያውም ከበረት አጣሪ (አጥር) እንደ ተሰባበረ ርግጋፊ ኾኑ፡፡ إِ‍نّ‍‍َ‍‍ا‍ أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ صَيْحَة‍‍‍ً وَا‍حِدَة‍‍‍ً فَكَانُو‍‍ا‍ كَهَش‍‍ِ‍ي‍مِ ا‍لْمُحْتَظِرِ
Wa Laqad Yassarnā Al-Qur'āna Lildhdhikri Fahal Min Muddakirin 054-032 ቁርኣንንም ለመገንዘብ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን? وَلَقَ‍‍د‍ْ يَسَّرْنَا ا‍لْقُرْآنَ لِلذِّكْ‍‍ر‍ِ فَهَلْ مِ‍‍ن‍ْ مُدَّكِر‍ٍ
Kadhdhabat Qawmu Lūţin Bin-Nudhuri 054-033 የሉጥ ሕዝብ በአስፈራሪዎቹ አስተባበለች፡፡ كَذَّبَتْ قَوْمُ ل‍‍ُ‍و‍ط‍‍‍ٍ بِ‍‍ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍ُذُ‍ر‍ِ
'Innā 'Arsalnā `Alayhim Ĥāşibāan 'Illā 'Āla Lūţin Najjaynāhum Bisaĥarin 054-034 እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ላክን፡፡ የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ (እነርሱንስ) በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው፡፡ إِ‍نّ‍‍َ‍‍ا‍ أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ حَاصِبا‍ً إِلاَّ آلَ ل‍‍ُ‍و‍ط‍‍‍ٍ نَجَّيْنَاهُ‍‍م‍ْ بِسَحَر‍ٍ
Ni`matan Min `Indinā Kadhālika Najzī Man Shakara 054-035 ከእኛ በኾነ ጸጋ (አዳንናቸው)፡፡ እንደዚሁ ያመሰገነን ሰው እንመነዳለን፡፡ نِعْمَة‍‍‍ً مِنْ عِ‍‍ن‍‍ْدِنَا كَذَلِكَ نَ‍‍ج‍‍ْزِي مَ‍‍ن‍ْ شَكَرَ
Wa Laqad 'Andharahum Baţshatanā Fatamāraw Bin-Nudhuri 054-036 ብርቱይቱን አያያዛችንንም በእርግጥ አስጠነቀቃቸው፡፡ በማስጠንቀቂያዎቹም ተከራከሩ፡፡ وَلَقَ‍‍د‍ْ أَن‍ذَرَهُ‍‍م‍ْ بَ‍‍ط‍‍ْشَتَنَا فَتَمَارَوْا بِ‍‍ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍ُذُ‍ر‍ِ
Wa Laqad Rāwadūhu `An Đayfihi Faţamasnā 'A`yunahum Fadhūqū `Adhābī Wa Nudhuri 054-037 ከእንግዶቹም እንዲያስመቻቸው ደጋግመው ፈለጉት፡፡ ወዲያውም ዓይኖቻቸውን አበስን፡፡ آ«ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎቼንም ቅመሱآ» (አልናቸው)፡፡ وَلَقَ‍‍د‍ْ رَاوَد‍ُو‍هُ عَ‍‍ن‍ْ ضَيْفِهِ فَطَمَسْنَ‍‍ا‍ أَعْيُنَهُمْ فَذُوقُو‍‍ا‍ عَذَابِي وَنُذُ‍ر‍ِ
Wa Laqad Şabbaĥahum Bukratan `Adhābun Mustaqirrun 054-038 በማለዳም ዘውታሪ የኾነ ቅጣት በእርግጥ ማለደባቸው፡፡ وَلَقَ‍‍د‍ْ صَبَّحَهُ‍‍م‍ْ بُكْرَةً عَذ‍َا‍ب‍‍‍ٌ مُسْتَقِرّ‍ٌ
Fadhūqū `Adhābī Wa Nudhuri 054-039 آ«ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎቼንም ቅመሱآ» (ተባሉ)፡፡ فَذُوقُو‍‍ا‍ عَذَابِي وَنُذُ‍ر‍ِ
Wa Laqad Yassarnā Al-Qur'āna Lildhdhikri Fahal Min Muddakirin 054-040 ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን? وَلَقَ‍‍د‍ْ يَسَّرْنَا ا‍لْقُرْآنَ لِلذِّكْ‍‍ر‍ِ فَهَلْ مِ‍‍ن‍ْ مُدَّكِر‍ٍ
Wa Laqad Jā'a 'Āla Fir`awna An-Nudhuru 054-041 የፈርዖንንም ቤተሰቦች ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጡዋቸው፡፡ وَلَقَ‍‍د‍ْ ج‍‍َ‍ا‍ءَ آلَ فِرْعَوْنَ ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍ُذُرُ
Kadhdhabū Bi'āyātinā Kullihā Fa'akhadhnāhum 'Akhdha `Azīzin Muqtadirin 054-042 በተዓምራቶቻችን በሁሏም አስተባበሉ፡፡ የብርቱ ቻይንም አያያዝ ያዝናቸው፡፡ كَذَّبُو‍‍ا‍ بِآيَاتِنَا كُلِّهَا فَأَخَذْنَاهُمْ أَخْذَ عَز‍ِي‍ز‍ٍ مُ‍‍ق‍‍ْتَدِر‍ٍ
'Akuffārukum Khayrun Min 'Ūla'ikum 'Am Lakum Barā'atun Az-Zuburi 054-043 ከሓዲዎቻችሁ ከእነዚህ በላጮች ናቸውን? ወይስ ለናንተ በመጽሐፎች ውስጥ (የተነገረ) ነፃነት አላችሁን? أَكُفَّارُكُمْ خَيْر‍ٌ مِنْ أ‍ُ‍وْلَئِكُمْ أَمْ لَكُ‍‍م‍ْ بَر‍َا‍ءَة‍‍‍ٌ فِي ا‍لزُّبُ‍‍ر‍ِ
'Am Yaqūlūna Naĥnu Jamī`un Muntaşirun 054-044 ወይስ آ«እኛ የተረዳን ክምቹዎች ነንآ» ይላሉን? أَمْ يَقُول‍‍ُ‍و‍نَ نَحْنُ جَم‍‍ِ‍ي‍ع‍‍‍ٌ مُ‍‍ن‍‍ْتَصِر‍ٌ
Sayuhzamu Al-Jam`u Wa Yuwallūna Ad-Dubura 054-045 ክምቹዎቹ በእርግጥ ድል ይምመታሉ፡፡ ጀርባዎችንም ያዞራሉ፡፡ سَيُهْزَمُ ا‍لْجَمْعُ وَيُوَلّ‍‍ُ‍و‍نَ ا‍لدُّبُرَ
Bali As-Sā`atu Maw`iduhum Wa As-Sā`atu 'Ad/há Wa 'Amarru 054-046 ይልቁንም ሰዓቲቱ (ትንሣኤ) ቀጠሮዋቸው ናት፡፡ ሰዓቲቱም በጣም የከበደችና የመረረች ናት፡፡ بَلِ ا‍لسَّاعَةُ مَوْعِدُهُمْ وَا‍لسَّاعَةُ أَ‍د‍‍ْهَى وَأَمَرُّ
'Inna Al-Mujrimīna Fī Đalālin Wa Su`urin 054-047 አመጸኞች በስህተትና በእሳቶች ውስጥ ናቸው፡፡ إِ‍نّ‍‍َ ا‍لْمُ‍‍ج‍‍ْ‍‍ر‍‍ِم‍‍ِ‍ي‍نَ فِي ضَلاَل‍‍‍ٍ وَسُعُر‍ٍ
Yawma Yusĥabūna Fī An-Nāri `Alá Wujūhihim Dhūqū Massa Saqara 054-048 በእሳት ውስጥ በፊቶቻቸው በሚጎተቱበት ቀን آ«የሰቀርን መንካት ቅመሱآ» (ይባላሉ)፡፡ يَوْمَ يُسْحَب‍‍ُ‍و‍نَ فِي ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َ‍ا‍ر‍ِ عَلَى وُجُوهِهِمْ ذُوقُو‍‍ا‍ مَسَّ سَقَرَ
'Innā Kulla Shay'in Khalaqnāhu Biqadarin 054-049 እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው፡፡ إِ‍نّ‍‍َا كُلَّ شَيْءٍ خَلَ‍‍ق‍‍ْن‍‍َ‍ا‍هُ بِقَدَر‍ٍ
Wa Mā 'Amrunā 'Illā Wāĥidatun Kalamĥin Bil-Başari 054-050 ትእዛዛችንም እንደ ዓይን ቅጽበት አንዲት (ቃል) እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ وَمَ‍‍ا‍ أَمْرُنَ‍‍ا إِلاَّ وَا‍حِدَة‍‍‍ٌ كَلَمْح‍‍‍ٍ بِ‍‍ا‍لْبَصَ‍‍ر‍ِ
Wa Laqad 'Ahlaknā 'Ashyā`akum Fahal Min Muddakirin 054-051 ብጤዎቻችሁንም በእርግጥ አጠፋን፡፡ ተገሳጭም አልለን? وَلَقَ‍‍د‍ْ أَهْلَكْنَ‍‍ا‍ أَشْيَاعَكُمْ فَهَلْ مِ‍‍ن‍ْ مُدَّكِر‍ٍ
Wa Kullu Shay'in Fa`alūhu Fī Az-Zuburi 054-052 የሠሩትም ነገር ሁሉ በመጽሐፎች ውስጥ ነው፡፡ وَكُلُّ شَيْء‍ٍ فَعَل‍‍ُ‍و‍هُ فِي ا‍لزُّبُ‍‍ر‍ِ
Wa Kullu Şaghīrin Wa Kabīrin Mustaţarun 054-053 ትንሹም ትልቁም ሁሉ የተጻፈ ነው፡፡ وَكُلُّ صَغ‍‍ِ‍ي‍ر‍ٍ وَكَب‍‍ِ‍ي‍ر‍ٍ مُسْتَطَر‍ٌ
'Inna Al-Muttaqīna Fī Jannātin Wa Naharin 054-054 አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በወንዞች ውስጥ ናቸው፡፡ إِ‍نّ‍‍َ ا‍لْمُتَّق‍‍ِ‍ي‍نَ فِي جَ‍‍ن‍ّ‍‍َ‍ا‍ت‍‍‍ٍ وَنَهَر‍ٍ
Fī Maq`adi Şidqin `Inda Malīkin Muqtadirin 054-055 (እነርሱም ውድቅ ቃልና መውወንጀል በሌለበት) በእውነት መቀመጫ ውስጥ ቻይ የሆነው ንጉሥ ዘንድ ናቸው፡፡ فِي مَ‍‍ق‍‍ْعَدِ صِ‍‍د‍‍ْقٍ عِ‍‍ن‍‍ْدَ مَل‍‍ِ‍ي‍ك‍‍‍ٍ مُ‍‍ق‍‍ْتَدِر‍ٍ
Next Sūrah