55) Sūrat Ar-Raĥmān

Printed format

55) سُورَة الرَّحمَان

Ar-Raĥmānu 055-001 አል-ረሕማን፤ ا‍لرَّحم‍‍َ‍ا‍نُ
`Allama Al-Qur'āna 055-002 ቁርኣንን አስተማረ፡፡ عَلَّمَ ا‍لْقُرْآنَ
Khalaqa Al-'Insāna 055-003 ሰውን ፈጠረ፡፡ خَلَقَ ا‍لإِن‍س‍‍َ‍ا‍نَ
`Allamahu Al-Bayāna 055-004 መናገርን አስተማረው፡፡ عَلَّمَهُ ا‍لْبَي‍‍َ‍ا‍نَ
Ash-Shamsu Wa Al-Qamaru Biĥusbānin 055-005 ፀሐይና ጨረቃ በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፡፡ ا‍لشَّمْسُ وَا‍لْقَمَرُ بِحُسْب‍‍َ‍ا‍ن‍‍‍ٍ
Wa An-Najmu Wa Ash-Shajaru Yasjudāni 055-006 ሐረግና ዛፍም (ለእርሱ) ይሰግዳሉ፡፡ وَال‍‍ن‍ّ‍‍َ‍‍ج‍‍ْمُ وَا‍لشَّجَرُ يَسْجُد‍َا‍نِ
Wa As-Samā'a Rafa`ahā Wa Wađa`a Al-Mīzāna 055-007 ሰማይንም አጓናት፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡ وَالسَّم‍‍َ‍ا‍ءَ رَفَعَهَا وَوَضَعَ ا‍لْمِيز‍َا‍نَ
'Allā Taţghaw Fī Al-Mīzāni 055-008 በሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ፡፡ أَلاَّ تَ‍‍ط‍‍ْغَوْا فِي ا‍لْمِيز‍َا‍نِ
Wa 'Aqīmū Al-Wazna Bil-Qisţi Wa Lā Tukhsirū Al-Mīzāna 055-009 መመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ፡፡ وَأَقِيمُو‍‍ا‍ ا‍لْوَزْنَ بِ‍‍ا‍لْقِسْطِ وَلاَ تُخْسِرُوا‍ ا‍لْمِيز‍َا‍نَ
Wa Al-'Arđa Wađa`ahā Lil'anāmi 055-010 ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት፡፡ وَالأَرْضَ وَضَعَهَا لِلأَن‍‍َ‍ا‍مِ
Fīhā Fākihatun Wa An-Nakhlu Dhātu Al-'Akmāmi 055-011 በውስጧ እሸት ባለ ሺፋኖች የኾኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትኾን፡፡ فِيهَا فَاكِهَة‍‍‍ٌ وَا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َخْلُ ذ‍َا‍تُ ا‍لأَكْم‍‍َ‍ا‍مِ
Wa Al-Ĥabbu Dhū Al-`Aşfi Wa Ar-Rayĥānu 055-012 የገለባ ባለቤት የኾነ ቅንጣትም፡፡ ባለ መልካም መዐዛ ቅጠሎችም (ያሉባት ስትኾን)፡፡ وَالْحَبُّ ذُو ا‍لْعَصْفِ وَا‍لرَّيْح‍‍َ‍ا‍نُ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-013 (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Khalaqa Al-'Insāna Min Şalşālin Kālfakhkhāri 055-014 ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው፡፡ خَلَقَ ا‍لإِن‍س‍‍َ‍ا‍نَ مِ‍‍ن‍ْ صَلْص‍‍َ‍ا‍ل‍‍‍ٍ كَالْفَخّ‍‍َ‍ا‍ر‍ِ
Wa Khalaqa Al-Jānna Minrijin Min Nārin 055-015 ጃንንም ከእሳት ከኾነ ነበልባል ፈጠረው፡፡ وَخَلَقَ ا‍لْج‍‍َ‍ا‍نّ‍‍َ مِ‍‍ن‍ْ مَا‍ر‍‍ِج‍‍‍ٍ مِ‍‍ن‍ْ ن‍‍َ‍ا‍ر‍ٍ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-016 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Rabbu Al-Mashriqayni Wa Rabbu Al-Maghribayni 055-017 የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ፤ የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው፡፡ رَبُّ ا‍لْمَشْ‍‍ر‍‍ِقَيْنِ وَرَبُّ ا‍لْمَغْ‍‍ر‍‍ِبَيْنِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-018 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Maraja Al-Baĥrayni Yaltaqiyāni 055-019 ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡ مَرَجَ ا‍لْبَحْرَيْنِ يَلْتَقِي‍‍َ‍ا‍نِ
Baynahumā Barzakhun Lā Yabghiyāni 055-020 (እንዳይዋሐዱ) በመካከላቸው ጋራጅ አልለ፡፡ (አንዱ ባንዱ ላይ) ወሰን አያልፉም፡፡ بَيْنَهُمَا بَرْزَخ‍‍‍ٌ لاَ يَ‍‍ب‍‍ْغِي‍‍َ‍ا‍نِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-021 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?â€؛ فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Yakhruju Minhumā Al-Lu'ulu'uu Wa Al-Marjānu 055-022 ሉልና መርጃን ከሁለቱ ይወጣል፡፡ يَخْرُجُ مِنْهُمَا ا‍للُّؤْلُؤُ وَا‍لْمَرْج‍‍َ‍ا‍نُ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-023 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Wa Lahu Al-Jawāri Al-Munsha'ātu Fī Al-Baĥri Kāl'a`lāmi 055-024 እንደ ጋራዎች ኾነው በባሕር ውስጥ የተሠሩት ተንሻለዮቹም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው፡፡ وَلَهُ ا‍لْجَو‍َا‍ر‍ِ ا‍لْمُ‍‍ن‍شَآتُ فِي ا‍لْبَحْ‍‍ر‍ِ كَالأَعْلاَمِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-025 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Kullu Man `Alayhā Fānin 055-026 በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡ كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا ف‍‍َ‍ا‍ن‍‍‍ٍ
Wa Yabqá Wajhu Rabbika Dhū Al-Jalāli Wa Al-'Ikrāmi 055-027 የልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡ وَيَ‍‍ب‍‍ْقَى وَج‍‍ْهُ رَبِّكَ ذُو ا‍لْجَلاَلِ وَا‍لإِكْر‍َا‍مِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-028 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Yas'aluhu Man As-Samāwāti Wa Al-'Arđi Kulla Yawmin Huwa Fī Sha'nin 055-029 በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል፡፡ በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው፡፡ يَسْأَلُهُ مَ‍‍ن‍ْ فِي ا‍لسَّمَاو‍َا‍تِ وَا‍لأَرْضِ كُلَّ يَوْمٍ هُوَ فِي شَأْن‍‍‍ٍ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-030 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?â€؛ فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Sanafrughu Lakum 'Ayyuhā Ath-Thaqalāni 055-031 እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ (መቆጣጠር) በእርግጥ እናስባለን፡፡ سَنَفْرُغُ لَكُمْ أَيُّهَا ا‍لثَّقَلاَنِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-032 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Yā Ma`shara Al-Jinni Wa Al-'Insi 'Ini Astaţa`tum 'An Tanfudhū Min 'Aqţāri As-Samāwāti Wa Al-'Arđi Fānfudhū Lā Tanfudhūna 'Illā Bisulţānin 055-033 የጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፡፡ በስልጣን እንጅ አትወጡም፡፡ (ግን ስልጣን የላችሁም) يَامَعْشَرَ ا‍لْجِ‍‍ن‍ّ‍‍ِ وَا‍لإِن‍سِ إِنِ ا‍سْتَطَعْتُمْ أَ‍ن‍ْ تَ‍‍ن‍فُذُوا‍ مِنْ أَ‍ق‍‍ْط‍‍َ‍ا‍ر‍ِ ا‍لسَّمَاو‍َا‍تِ وَا‍لأَرْضِ فَان‍فُذُوا‍ لاَ تَ‍‍ن‍فُذ‍ُو‍نَ إِلاَّ بِسُلْط‍‍َ‍ا‍ن‍‍‍ٍ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-034 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Yursalu `Alaykumā Shuwāžun Min Nārin Wa Nuĥāsun Falā Tantaşirāni 055-035 በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል፣ ጭስም ይላክባችኋል፡፡ (ሁለታችሁም) አትርረዱምም፡፡ يُرْسَلُ عَلَيْكُمَا شُو‍َا‍ظ‍‍‍ٌ مِ‍‍ن‍ْ ن‍‍َ‍ا‍ر‍ٍ وَنُح‍‍َ‍ا‍س‍‍‍ٌ فَلاَ تَ‍‍ن‍تَصِر‍َا‍نِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-036 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Fa'idhā Anshaqqati As-Samā'u Fakānat Wardatan Kālddihāni 055-037 ሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፣ እንደታረበ ቆዳ በኾነች ጊዜ፤ (ጭንቁን ምን አበረታው)፡፡ فَإِذَا ا‍ن‍شَقَّتِ ا‍لسَّم‍‍َ‍ا‍ءُ فَكَانَتْ وَرْدَة‍‍‍ً كَال‍دِّه‍‍َ‍ا‍نِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-038 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Fayawma'idhin Lā Yus'alu `An Dhanbihi 'Insun Wa Lā Jānnun 055-039 በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም፡፡ فَيَوْمَئِذ‍ٍ لاَ يُسْأَلُ عَ‍‍ن‍ْ ذَ‍ن‍‍ْبِهِ إِن‍س‍‍‍ٌ وَلاَ ج‍‍َ‍ا‍نّ‍‍‍ٌ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-040 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Yu`rafu Al-Mujrimūna Bisīmāhum Fayu'ukhadhu Bin-Nawāşī Wa Al-'Aqdāmi 055-041 ከሓዲዎች በምልክታቸው ይታወቃሉ፡፡ አናቶቻቸውንና ጫማዎቻቸውንም ይያዛሉ፡፡ يُعْرَفُ ا‍لْمُ‍‍ج‍‍ْ‍‍ر‍‍ِم‍‍ُ‍و‍نَ بِسِيمَاهُمْ فَيُؤْخَذُ بِ‍‍ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َوَاصِي وَا‍لأَ‍ق‍‍ْد‍َا‍مِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-042 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ፡፡ فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Hadhihi Jahannamu Allatī Yukadhdhibu Bihā Al-Mujrimūna 055-043 ይህቺ ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት (ይባላሉ)፡፡ هَذِهِ جَهَ‍‍ن‍ّ‍‍َمُ ا‍لَّتِي يُكَذِّبُ بِهَا ا‍لْمُ‍‍ج‍‍ْ‍‍ر‍‍ِم‍‍ُ‍و‍نَ
Yaţūfūna Baynahā Wa Bayna Ĥamīmin 'Ānin 055-044 በእርሷና በጣም ሞቃት በኾነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ፡፡ يَطُوف‍‍ُ‍و‍نَ بَيْنَهَا وَبَيْنَ حَم‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٍ آن‍‍‍ٍ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-045 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Wa Liman Khāfa Maqāma Rabbihi Jannatāni 055-046 በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡ وَلِمَنْ خ‍‍َ‍ا‍فَ مَق‍‍َ‍ا‍مَ رَبِّهِ جَ‍‍ن‍ّ‍‍َت‍‍َ‍ا‍نِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-047 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Dhawātā 'Afnānin 055-048 የቀንዘሎች ባለ ቤቶች የኾኑ (ገነቶች አልሉት)፡፡ ذَوَاتَ‍‍ا‍ أَفْن‍‍َ‍ا‍ن‍‍‍ٍ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-049 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Fīhimā `Aynāni Tajriyāni 055-050 በሁለቱ ውስጥ የሚፈስሱ ሁለት ምንጮች አልሉ፡፡ فِيهِمَا عَيْن‍‍َ‍ا‍نِ تَ‍‍ج‍‍ْ‍‍ر‍‍ِي‍‍َ‍ا‍نِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-051 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Fīhimā Min Kulli Fākihatin Zawjāni 055-052 በሁለቱ ውስጥ ከፍራፍሬዎች ሁሉ ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አልሉ፡፡ فِيهِمَا مِ‍‍ن‍ْ كُلِّ فَاكِهَة‍‍‍ٍ زَوْج‍‍َ‍ا‍نِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-053 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Muttaki'īna `Alá Furushin Baţā'inuhā Min 'Istabraqin Wa Janá Al-Jannatayni Dānin 055-054 የውስጥ ጉስጉሳቸው ከወፍራም ሐር በኾኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቹ ሲኾኑ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ (ለለቃሚ) ቅርብ ነው፡፡ مُتَّكِئ‍‍ِ‍ي‍نَ عَلَى فُرُش‍‍‍ٍ بَط‍‍َ‍ا‍ئِنُهَا مِ‍‍ن‍ْ إِسْتَ‍‍ب‍‍ْرَق‍‍‍ٍ وَجَنَى ا‍لْجَ‍‍ن‍ّ‍‍َتَيْنِ د‍َا‍ن‍‍‍ٍ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-055 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Fīhinna Qāşirātu Aţ-Ţarfi Lam Yaţmithhunna 'Insun Qablahum Wa Lā Jānnun 055-056 በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጃንም ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡ فِيهِ‍‍ن‍ّ‍‍َ قَاصِر‍َا‍تُ ا‍لطَّرْفِ لَمْ يَ‍‍ط‍‍ْمِثْهُ‍‍ن‍ّ‍‍َ إِ‍ن‍‍ْس‍‍‍ٌ قَ‍‍ب‍‍ْلَهُمْ وَلاَ ج‍‍َ‍ا‍نّ‍‍‍ٌ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-057 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Ka'annahunna Al-Yāqūtu Wa Al-Marjānu 055-058 ልክ ያቁትና መርጃን ይመስላሉ፡፡ كَأَ‍نّ‍‍َهُ‍‍ن‍ّ‍‍َ ا‍لْيَاق‍‍ُ‍و‍تُ وَا‍لْمَرْج‍‍َ‍ا‍نُ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-059 ከጌታችሁም ጸጋዎቸ በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Hal Jazā'u Al-'Iĥsāni 'Illā Al-'Iĥsānu 055-060 የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን? هَلْ جَز‍َا‍ءُ ا‍لإِحْس‍‍َ‍ا‍نِ إِلاَّ ا‍لإِحْس‍‍َ‍ا‍نُ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-061 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Wa Min Dūnihimā Jannatāni 055-062 ከሁለቱ ገነቶችም ሌላ ሁለት ገነቶች አልሉ፡፡ وَمِ‍‍ن‍ْ دُونِهِمَا جَ‍‍ن‍ّ‍‍َت‍‍َ‍ا‍نِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-063 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?â€؛ فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Mud/hāmmatāni 055-064 ከልምላሜያቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው፡፡ مُ‍‍د‍‍ْه‍‍َ‍ا‍مّ‍‍َت‍‍َ‍ا‍نِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-065 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Fīhimā `Aynāni Nađđākhatāni 055-066 በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አልሉ፡፡ فِيهِمَا عَيْن‍‍َ‍ا‍نِ نَضَّاخَت‍‍َ‍ا‍نِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-067 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Fīhimā Fākihatun Wa Nakhlun Wa Rummānun 055-068 በውስጣቸው ፍራፍሬ፣ ዘምባባም፣ ሩማንም አልለ፡፡ فِيهِمَا فَاكِهَة‍‍‍ٌ وَنَخْل‍‍‍ٌ وَرُ‍مّ‍‍َ‍ا‍ن‍‍‍ٌ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-069 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Fīhinna Khayrātun Ĥisānun 055-070 በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልክ ውቦች (ሴቶች) አልሉ፡፡ فِيهِ‍‍ن‍ّ‍‍َ خَيْر‍َا‍تٌ حِس‍‍َ‍ا‍ن‍‍‍ٌ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-071 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Ĥūrun Maqşūrātun Al-Khiyāmi 055-072 በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡ ح‍ُو‍ر‍ٌ مَ‍‍ق‍‍ْصُور‍َا‍ت‍‍‍ٌ فِي ا‍لْخِي‍‍َ‍ا‍مِ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-073 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Lam Yaţmithhunna 'Insun Qablahum Wa Lā Jānnun 055-074 ከነርሱ በፊት ሰውም ጃንም አልገሰሳቸውም፡፡ لَمْ يَ‍‍ط‍‍ْمِثْهُ‍‍ن‍ّ‍‍َ إِن‍س‍‍‍ٌ قَ‍‍ب‍‍ْلَهُمْ وَلاَ ج‍‍َ‍ا‍نّ‍‍‍ٌ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-075 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባበላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Muttaki'īna `Alá Rafrafin Khrin Wa `Abqarīyin Ĥisānin 055-076 በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲኾኑ (ይቀመጣሉ)፡፡ مُتَّكِئ‍‍ِ‍ي‍نَ عَلَى رَفْرَفٍ خُضْر‍ٍ وَعَ‍‍ب‍‍ْقَ‍‍ر‍‍ِيٍّ حِس‍‍َ‍ا‍ن‍‍‍ٍ
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni 055-077 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّب‍‍َ‍ا‍نِ
Tabāraka Asmu Rabbika Dhī Al-Jalāli Wa Al-'Ikrāmi 055-078 የግርማና የመክበር ባለቤት የኾነው ጌታህ ስም ተባረከ፡፡ تَبَارَكَ ا‍سْمُ رَبِّكَ ذِي ا‍لْجَلاَلِ وَا‍لإِكْر‍َا‍مِ
Next Sūrah