96) Sūrat Al-`Alaq

Printed format

96) سُورَة العَلَق

Aqra' Biāsmi Rabbika Al-Ladhī Khalaqa 096-001 አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡ ا‍ق‍‍ْرَأْ بِ‍ا‍سْمِ رَبِّكَ ا‍لَّذِي خَلَ‍‍ق‍َ
Khalaqa Al-'Insāna Min `Alaqin 096-002 ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡ خَلَقَ ا‍لإِن‍س‍‍َ‍ا‍نَ مِنْ عَلَ‍‍ق‍‍ٍ
Aqra' Wa Rabbuka Al-'Akramu 096-003 አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤ ا‍ق‍‍ْرَأْ وَرَبُّكَ ا‍لأَكْرَمُ
Al-Ladhī `Allama Bil-Qalami 096-004 ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡ ا‍لَّذِي عَلَّمَ بِ‍‍ا‍لْقَلَمِ
`Allama Al-'Insāna Mā Lam Ya`lam 096-005 ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡ عَلَّمَ ا‍لإِن‍س‍‍َ‍ا‍نَ مَا لَمْ يَعْلَمْ
Kallā 'Inna Al-'Insāna Layaţghá 096-006 በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡ كَلاَّ إِ‍نّ‍‍َ ا‍لإِن‍س‍‍َ‍ا‍نَ لَيَ‍‍ط‍‍ْغَى
'An Ra'āhu Astaghná 096-007 ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡ أَ‍ن‍ْ رَآهُ ا‍سْتَغْنَى
'Inna 'Ilá Rabbika Ar-Ruj 096-008 መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ إِ‍نّ‍‍َ إِلَى رَبِّكَ ا‍لرُّ‍‍ج‍‍ْعَى
'Ara'ayta Al-Ladhī Yanhá 096-009 አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡ أَرَأَيْتَ ا‍لَّذِي يَنْهَى
`Abdāan 'Idhā Şallá 096-010 ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤ عَ‍‍ب‍‍ْدا‍ً إِذَا صَلَّى
'Ara'ayta 'In Kāna `Alá Al-Hudá 096-011 አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤ أَرَأَيْتَ إِ‍ن‍ْ ك‍‍َ‍ا‍نَ عَلَى ا‍لْهُدَى
'Aw 'Amara Bit-Taq 096-012 ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤ أَوْ أَمَرَ بِ‍‍ا‍لتَّ‍‍ق‍‍ْوَى
'Ara'ayta 'In Kadhdhaba Wa Tawallá 096-013 አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤ أَرَأَيْتَ إِ‍ن‍ْ كَذَّبَ وَتَوَلَّى
'Alam Ya`lam Bi'anna Al-Laha Yará 096-014 አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን? أَلَمْ يَعْلَ‍‍م‍ْ بِأَ‍نّ‍‍َ ا‍للَّهَ يَرَى
Kallā La'in Lam Yantahi Lanasfa`ā Bin-Nāşiyahi 096-015 ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡ كَلاَّ لَئِ‍‍ن‍ْ لَمْ يَ‍‍ن‍‍ْتَهِ لَنَسْفَعَا بِ‍‍ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َاصِيَةِ
Nāşiyatindhibatin Khāţi'ahin 096-016 ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡ نَاصِيَة‍‍‍ٍ كَاذِبَةٍ خَاطِئَة‍‍‍ٍ
Falyad`u Nādiyah 096-017 ሸንጎውንም ይጥራ፡፡ فَلْيَ‍‍د‍‍ْعُ نَادِيَه
Sanad`u Az-Zabāniyaha 096-018 (እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡ سَنَ‍‍د‍‍ْعُ ا‍لزَّبَانِيَةَ
Kallā Lā Tuţi`hu Wa Asjudqtarib 096-019 ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡ كَلاَّ لاَ تُطِعْهُ وَا‍سْجُ‍‍د‍ْ وَا‍ق‍‍ْتَ‍‍ر‍‍ِ‍ب‍ْ
Next Sūrah