80) Sūrat `Abasa

Printed format

80) سُورَة عَبَسَ

`Abasa Wa Tawallá 080-001 ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፡፡ عَبَسَ وَتَوَلَّى
'An Jā'ahu Al-'A`má 080-002 ዕውሩ ስለ መጣው፡፡ أَ‍ن‍ْ ج‍‍َ‍ا‍ءَهُ ا‍لأَعْمَى
Wa Mā Yudrīka La`allahu Yazzakká 080-003 ምን ያሳውቅሃል? (ከኀጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል፡፡ وَمَا يُ‍‍د‍‍ْ‍ر‍‍ِي‍كَ لَعَلَّهُ يَزَّكَّى
'Aw Yadhdhakkaru Fatanfa`ahu Adh-Dhikrá 080-004 ወይም ሊገሠጽ ግሠጼይቱም ልትጠቅመው (ይከጀላል)፡፡ أَوْ يَذَّكَّرُ فَتَ‍‍ن‍‍ْفَعَهُ ا‍لذِّكْرَى
'Ammā Mani Astaghná 080-005 የተብቃቃው ሰውማ፤ أَ‍مّ‍‍َا مَنِ ا‍سْتَغْنَى
Fa'anta Lahu Taşaddá 080-006 አንተ ለእርሱ (ለእምነቱ በመጓጓት) በፈገግታ ትቀበለዋለህ፡፡ فَأَ‍ن‍‍ْتَ لَهُ تَصَدَّى
Wa Mā `Alayka 'Allā Yazzakká 080-007 ባይጥራራ (ባያምን) ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትኾን፡፡ وَمَا عَلَيْكَ أَلاَّ يَزَّكَّى
Wa 'Ammā Man Jā'aka Yas`á 080-008 እየገሰገሰ የመጣህ ሰውማ፤ وَأَ‍مّ‍‍َا مَ‍‍ن‍ْ ج‍‍َ‍ا‍ءَكَ يَسْعَى
Wa Huwa Yakhshá 080-009 እርሱ (አላህን) የሚፈራ ሲኾን፤ وَهُوَ يَخْشَى
Fa'anta `Anhu Talahhá 080-010 አንተ ከእርሱ ትዝዘናጋለህ፡፡ فَأَ‍ن‍‍ْتَ عَنْهُ تَلَهَّى
Kallā 'Innahā Tadhkirahun 080-011 ተከልከል፡፡ እርሷ ማስገንዘቢያ ናት፡፡ كَلاَّ إِ‍نّ‍‍َهَا تَذْكِرَة‍‍‍ٌ
Faman Shā'a Dhakarahu 080-012 የሻም ሰው (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል፡፡ فَمَ‍‍ن‍ْ ش‍‍َ‍ا‍ءَ ذَكَرَهُ
Fī Şuĥufin Mukarramahin 080-013 በተከበሩ ጽሑፎች ውስጥ ነው፡፡ فِي صُحُف‍‍‍ٍ مُكَرَّمَة‍‍‍ٍ
Marfū`atin Muţahharahin 080-014 ከፍ በተደረገች ንጹሕ በተደረገች (ጽሑፍ ውስጥ ነው)፡፡ مَرْفُوعَة‍‍‍ٍ مُطَهَّرَة‍‍‍ٍ
Bi'aydī Safarahin 080-015 በጸሐፊዎቹ (መላእክት) እጆች (ንጹሕ የተደረገች)፡፡ بِأَيْدِي سَفَرَة‍‍‍ٍ
Kirāmin Bararahin 080-016 የተከበሩና ታዛዦች በኾኑት (ጸሐፊዎች እጆች)፡፡ كِر‍َا‍م‍‍‍ٍ بَرَرَة‍‍‍ٍ
Qutila Al-'Insānu Mā 'Akfarahu 080-017 ሰው ተረገመ፤ ምን ከሓዲ አደረገው? قُتِلَ ا‍لإِ‍ن‍‍ْس‍‍َ‍ا‍نُ مَ‍‍ا‍ أَكْفَرَهُ
Min 'Ayyi Shay'in Khalaqahu 080-018 (ጌታው) በምን ነገር ፈጠረው? (አያስብምን?) مِنْ أَيِّ شَيْءٍ خَلَقَهُ
Min Nuţfatin Khalaqahu Faqaddarahu 080-019 ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነውም፡፡ مِ‍‍ن‍ْ نُ‍‍ط‍‍ْفَةٍ خَلَقَهُ فَقَدَّرَهُ
Thumma As-Sabīla Yassarahu 080-020 ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው፡፡ ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ ا‍لسَّب‍‍ِ‍ي‍لَ يَسَّرَهُ
Thumma 'Amātahu Fa'aqbarahu 080-021 ከዚያም ገደለው፤ እንዲቀበርም አደረገው፡፡ ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ أَمَاتَهُ فَأَ‍ق‍‍ْبَرَهُ
Thumma 'Idhā Shā'a 'Ansharahu 080-022 ከዚያም (ማንሳቱን) በሻ ጊዜ ያስነሳዋል፡፡ ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ إِذَا ش‍‍َ‍ا‍ءَ أَ‍ن‍‍ْشَرَهُ
Kallā Lammā Yaqđi Mā 'Amarahu 080-023 በእውነት ያንን (ጌታው) ያዘዘውን ገና አልፈጸመም፡፡ كَلاَّ لَ‍‍م‍ّ‍‍َا يَ‍‍ق‍‍ْضِ مَ‍‍ا‍ أَمَرَهُ
Falyanžuri Al-'Insānu 'Ilá Ţa`āmihi 080-024 ሰውም ወደ ምግቡ ይመልከት፡፡ فَلْيَ‍‍ن‍‍ْظُ‍‍ر‍ِ ا‍لإِن‍س‍‍َ‍ا‍نُ إِلَى طَعَامِهِ
'Annā Şabab Al-Mā'a Şaban 080-025 እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መኾናችንን፡፡ أَ‍نّ‍‍َا صَبَ‍‍ب‍‍ْنَا ا‍لْم‍‍َ‍ا‍ءَ صَبّا‍ً
Thumma Shaqaq Al-'Arđa Shaqan 080-026 ከዚያም ምድርን (በደካማ ቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤ ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ شَقَ‍‍ق‍‍ْنَا ا‍لأَرْضَ شَقّا‍ً
Fa'anbatnā Fīhā Ĥaban 080-027 በውስጧም እኽልን ያበቀልን፤ فَأَ‍ن‍‍ْبَتْنَا فِيهَا حَبّا‍ً
Wa `Inabāan Wa Qađbāan 080-028 ወይንንም፤ እርጥብ ያበቀልን፤ وَعِنَبا‍ً وَقَضْبا‍ً
Wa Zaytūnāan Wa Nakhan 080-029 የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤ وَزَيْتُونا‍ً وَنَخْلا‍ً
Wa Ĥadā'iqa Ghulbāan 080-030 ጭፍቆች አትክልቶችንም፤ وَحَد‍َا‍ئِقَ غُلْبا‍ً
Wa Fākihatan Wa 'Aban 080-031 ፍራፍሬንም ገለባንም፤ (ያበቀልን መኾናችንን ይመልከት)፡፡ وَفَاكِهَة‍‍‍ً وَأَبّا‍ً
Matā`āan Lakum Wa Li'an`āmikum 080-032 ለእናንተም ለእንስሶቻችሁም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን ሠራን)፡፡ مَتَاعا‍ً لَكُمْ وَلِأَنْعَامِكُمْ
Fa'idhā Jā'ati Aş-Şākhkhahu 080-033 አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤ فَإِذَا ج‍‍َ‍ا‍ءَتِ ا‍لصّ‍‍َ‍ا‍خَّةُ
Yawma Yafirru Al-Mar'u Min 'Akhīhi 080-034 ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤ يَوْمَ يَفِرُّ ا‍لْمَرْءُ مِنْ أَخ‍‍ِ‍ي‍هِ
Wa 'Ummihi Wa 'Abīhi 080-035 ከናቱም ካባቱም፤ وَأُ‍مّ‍‍ِهِ وَأَب‍‍ِ‍ي‍هِ
Wa Şāĥibatihi Wa Banīhi 080-036 ከሚስቱም ከልጁም፤ وَصَاحِبَتِهِ وَبَن‍‍ِ‍ي‍هِ
Likulli Amri'in Minhum Yawma'idhin Sha'nun Yughnīhi 080-037 ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ኹነታ አልለው፡፡ لِكُلِّ ا‍مْ‍‍ر‍‍ِئ‍‍‍ٍ مِنْهُمْ يَوْمَئِذ‍ٍ شَأْن‍‍‍ٌ يُغْن‍‍ِ‍ي‍هِ
Wujūhun Yawma'idhin Musfirahun 080-038 ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፤ وُج‍‍ُ‍و‍ه‍‍‍ٌ يَوْمَئِذ‍ٍ مُسْفِرَة‍‍‍ٌ
Đāĥikatun Mustabshirahun 080-039 ሳቂዎችም ተደሳቾችም ናቸው፡፡ ضَاحِكَة‍‍‍ٌ مُسْتَ‍‍ب‍‍ْشِرَة‍‍‍ٌ
Wa Wujūhun Yawma'idhin `Alayhā Ghabarahun 080-040 ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አልለባቸው፤ وَوُج‍‍ُ‍و‍ه‍‍‍ٌ يَوْمَئِذٍ عَلَيْهَا غَبَرَة‍‍‍ٌ
Tarhaquhā Qatarahun 080-041 ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤ تَرْهَقُهَا قَتَرَة‍‍‍ٌ
'Ūlā'ika Humu Al-Kafaratu Al-Fajarahu 080-042 እነዚያ እነሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡ أ‍ُ‍وْل‍‍َ‍ا‍ئِكَ هُمُ ا‍لْكَفَرَةُ ا‍لْفَجَرَةُ
Next Sūrah