70) Sūrat Al-Ma`ārij

Printed format

70) سُورَة المَعَارِج

Sa'ala Sā'ilun Bi`adhābin Wāqi`in 070-001 ወዳቂ ከኾነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ፡፡ سَأَلَ س‍‍َ‍ا‍ئِل‍‍‍ٌ بِعَذ‍َا‍ب‍‍‍ٍ وَا‍قِع‍‍‍ٍ
Lilkāfiryna Laysa Lahu Dāfi`un 070-002 በከሓዲዎች ላይ (ወዳቂ ከኾነው) ለእርሱ መላሽ የለውም፡፡ لِلْكَافِرينَ لَيْسَ لَهُ دَافِع‍‍‍ٌ
Mina Al-Lahi Dhī Al-Ma`āriji 070-003 የ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከኾነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡ مِنَ ا‍للَّهِ ذِي ا‍لْمَعَا‍ر‍‍ِ‍ج‍ِ
Ta`ruju Al-Malā'ikatu Wa Ar-Rūĥu 'Ilayhi Fī Yawmin Kāna Miqdāruhu Khamsīna 'Alfa Sanahin 070-004 መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤ (ይወጣሉ)፡፡ تَعْرُجُ ا‍لْمَلاَئِكَةُ وَا‍لرّ‍ُو‍حُ إِلَيْهِ فِي يَوْم‍‍‍ٍ ك‍‍َ‍ا‍نَ مِ‍‍ق‍‍ْدَارُهُ خَمْس‍‍ِ‍ي‍نَ أَلْفَ سَنَة‍‍‍ٍ
Fāşbir Şabrāan Jamīlāan 070-005 መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡ فَاصْبِرْ صَ‍‍ب‍‍ْرا‍ً جَمِيلا‍ً
'Innahum Yarawnahu Ba`īdāan 070-006 እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡ إِ‍نّ‍‍َهُمْ يَرَوْنَهُ بَعِيدا‍ً
Wa Narāhu Qarībāan 070-007 እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡ وَنَر‍َا‍هُ قَ‍‍ر‍‍ِيبا‍ً
Yawma Takūnu As-Samā'u Kālmuhli 070-008 ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡ يَوْمَ تَك‍‍ُ‍و‍نُ ا‍لسَّم‍‍َ‍ا‍ءُ كَالْمُهْلِ
Wa Takūnu Al-Jibālu Kāl`ihni 070-009 ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን፡፡ وَتَك‍‍ُ‍و‍نُ ا‍لْجِب‍‍َ‍ا‍لُ كَالْعِهْنِ
Wa Lā Yas'alu Ĥamīmun Ĥamīmāan 070-010 ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡ وَلاَ يَسْأَلُ حَم‍‍ِ‍ي‍مٌ حَمِيما‍ً
Yubaşşarūnahum Yawaddu Al-Mujrimu Law Yaftadī Min `Adhābi Yawmi'idhin Bibanīhi 070-011 (ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡ يُبَصَّرُونَهُمْ يَوَدُّ ا‍لْمُ‍‍ج‍‍ْ‍‍ر‍‍ِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذ‍َا‍بِ يَوْمِئِذ‍ٍ بِبَن‍‍ِ‍ي‍هِ
Wa Şāĥibatihi Wa 'Akhīhi 070-012 በሚስቱም በወንድሙም፡፡ وَصَاحِبَتِهِ وَأَخ‍‍ِ‍ي‍هِ
Wa Faşīlatihi Allatī Tu'uwyhi 070-013 በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡ وَفَصِيلَتِهِ ا‍لَّتِي تُؤْويهِ
Wa Man Al-'Arđi Jamī`āan Thumma Yunjīhi 070-014 በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡ وَمَ‍‍ن‍ْ فِي ا‍لأَرْضِ جَمِيعا‍ً ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ يُ‍‍ن‍ج‍‍ِ‍ي‍هِ
Kallā 'Innahā Lažá 070-015 ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡ كَلاَّ إِ‍نّ‍‍َهَا لَظَى
Nazzā`atan Lilshshawá 070-016 የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡ نَزَّاعَة‍‍‍ً لِلشَّوَى
Tad`ū Man 'Adbara Wa Tawallá 070-017 (ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡ تَ‍‍د‍‍ْعُو‍‍ا‍ مَنْ أَ‍د‍‍ْبَرَ وَتَوَلَّى
Wa Jama`a Fa'aw`á 070-018 ገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡ وَجَمَعَ فَأَوْعَى
'Inna Al-'Insāna Khuliqa Halū`āan 070-019 ሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡ إِ‍نّ‍‍َ ا‍لإِن‍س‍‍َ‍ا‍نَ خُلِقَ هَلُوعا‍ً
'Idhā Massahu Ash-Sharru Jazū`āan 070-020 ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡ إِذَا مَسَّهُ ا‍لشَّرُّ جَزُوعا‍ً
Wa 'Idhā Massahu Al-Khayru Manū`āan 070-021 መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡ وَإِذَا مَسَّهُ ا‍لْخَيْرُ مَنُوعا‍ً
'Illā Al-Muşallīna 070-022 ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡ إِلاَّ ا‍لْمُصَلّ‍‍ِ‍ي‍نَ
Al-Ladhīna Hum `Alá Şalātihim Dā'imūna 070-023 እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ هُمْ عَلَى صَلاَتِهِمْ د‍َا‍ئِم‍‍ُ‍و‍نَ
Wa Al-Ladhīna Fī 'Amwālihim Ĥaqqun Ma`lūmun 070-024 እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡ وَالَّذ‍ِي‍نَ فِ‍‍ي‍ أَمْوَالِهِمْ حَقّ‍‍‍ٌ مَعْل‍‍ُ‍و‍م‍‍‍ٌ
Lilssā'ili Wa Al-Maĥrūmi 070-025 ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡ لِلسّ‍‍َ‍ا‍ئِلِ وَا‍لْمَحْر‍ُو‍مِ
Wa Al-Ladhīna Yuşaddiqūna Biyawmi Ad-Dīni 070-026 እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡ وَالَّذ‍ِي‍نَ يُصَدِّق‍‍ُ‍و‍نَ بِيَوْمِ ا‍لدّ‍ِي‍نِ
Wa Al-Ladhīna Hum Min `Adhābi Rabbihim Mushfiqūna 070-027 እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡ وَالَّذ‍ِي‍نَ هُ‍‍م‍ْ مِنْ عَذ‍َا‍بِ رَبِّهِ‍‍م‍ْ مُشْفِق‍‍ُ‍و‍نَ
'Inna `Adhāba Rabbihim Ghayru Ma'mūnin 070-028 የጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡ إِ‍نّ‍‍َ عَذ‍َا‍بَ رَبِّهِمْ غَيْرُ مَأْم‍‍ُ‍و‍ن‍‍‍ٍ
Wa Al-Ladhīna Hum Lifurūjihim Ĥāfižūna 070-029 እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ وَالَّذ‍ِي‍نَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظ‍‍ُ‍و‍نَ
'Illā `Alá 'Azwājihim 'Aw Mā Malakat 'Aymānuhum Fa'innahum Ghayru Malūmīna 070-030 በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ إِلاَّ عَلَى أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِ‍نّ‍‍َهُمْ غَيْرُ مَلُوم‍‍ِ‍ي‍نَ
Famani Abtaghá Warā'a Dhālika Fa'ūlā'ika Humu Al-`Ādūna 070-031 ከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡ فَمَنِ ا‍ب‍‍ْتَغَى وَر‍َا‍ءَ ذَلِكَ فَأ‍ُ‍وْل‍‍َ‍ا‍ئِكَ هُمُ ا‍لْعَاد‍ُو‍نَ
Wa Al-Ladhīna Hum Li'mānātihim Wa `Ahdihim Rā`ūna 070-032 እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ وَالَّذ‍ِي‍نَ هُمْ لِأمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاع‍‍ُ‍و‍نَ
Wa Al-Ladhīna Hum Bishahādātihim Qā'imūna 070-033 እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡ وَالَّذ‍ِي‍نَ هُ‍‍م‍ْ بِشَهَادَاتِهِمْ ق‍‍َ‍ا‍ئِم‍‍ُ‍و‍نَ
Wa Al-Ladhīna Hum `Alá Şalātihim Yuĥāfižūna 070-034 እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡ وَالَّذ‍ِي‍نَ هُمْ عَلَى صَلاَتِهِمْ يُحَافِظ‍‍ُ‍و‍نَ
'Ūlā'ika Fī Jannātin Mukramūna 070-035 እነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡ أ‍ُ‍وْل‍‍َ‍ا‍ئِكَ فِي جَ‍‍ن‍ّ‍‍َ‍ا‍ت‍‍‍ٍ مُكْرَم‍‍ُ‍و‍نَ
Famāli Al-Ladhīna Kafarū Qibalaka Muhţi`īna 070-036 ለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው? فَم‍‍َ‍ا‍لِ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ كَفَرُوا‍ قِبَلَكَ مُهْطِع‍‍ِ‍ي‍نَ
`Ani Al-Yamīni Wa `Ani Ash-Shimāli `Izīna 070-037 ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡ عَنِ ا‍لْيَم‍‍ِ‍ي‍نِ وَعَنِ ا‍لشِّم‍‍َ‍ا‍لِ عِز‍ِي‍نَ
'Ayaţma`u Kullu Amri'in Minhum 'An Yudkhala Jannata Na`īmin 070-038 ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን? أَيَ‍‍ط‍‍ْمَعُ كُلُّ ا‍مْ‍‍ر‍‍ِئ‍‍‍ٍ مِنْهُمْ أَ‍ن‍ْ يُ‍‍د‍‍ْخَلَ جَ‍‍ن‍ّ‍‍َةَ نَع‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٍ
Kallā 'Innā Khalaqnāhum Mimmā Ya`lamūna 070-039 ይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡ كَلاَّ إِ‍نّ‍‍َا خَلَ‍‍ق‍‍ْنَاهُ‍‍م‍ْ مِ‍‍م‍ّ‍‍َا يَعْلَم‍‍ُ‍و‍نَ
Falā 'Uqsimu Birabbi Al-Mashāriqi Wa Al-Maghāribi 'Innā Laqādirūna 070-040 በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ فَلاَ أُ‍ق‍‍ْسِمُ بِرَبِّ ا‍لْمَشَا‍ر‍‍ِقِ وَا‍لْمَغَا‍ر‍‍ِبِ إِ‍نّ‍‍َا لَقَادِر‍ُو‍نَ
`Alá 'An Nubaddila Khayrāan Minhum Wa Mā Naĥnu Bimasbūqīna 070-041 ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡ عَلَى أَ‍ن‍ْ نُبَدِّلَ خَيْرا‍ً مِنْهُمْ وَمَا نَحْنُ بِمَسْبُوق‍‍ِ‍ي‍نَ
Fadharhum Yakhūđū Wa Yal`abū Ĥattá Yulāqū Yawmahumu Al-Ladhī Yū`adūna 070-042 ያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ ይዋኙ ይጫወቱም፡፡ فَذَرْهُمْ يَخُوضُو‍‍ا‍ وَيَلْعَبُو‍‍ا‍ حَتَّى يُلاَقُو‍‍ا‍ يَوْمَهُمُ ا‍لَّذِي يُوعَد‍ُو‍نَ
Yawma Yakhrujūna Mina Al-'Ajthi Sirā`āan Ka'annahum 'Ilá Nuşubin Yūfiđūna 070-043 ወደ ጣዖቶች እንደሚሽቀዳደሙ ኾነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን (እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው)፡፡ يَوْمَ يَخْرُج‍‍ُ‍و‍نَ مِنَ ا‍لأَ‍ج‍‍ْد‍َا‍ثِ سِرَاعا‍ً كَأَ‍نّ‍‍َهُمْ إِلَى نُصُب‍‍‍ٍ يُوفِض‍‍ُ‍و‍نَ
Khāshi`atan 'Abşāruhum Tarhaquhum Dhillatun Dhālika Al-Yawmu Al-Ladhī Kānū Yū`adūna 070-044 ዓይኖቻቸው ያፈሩ ኾነው ውርደት ትሸፍናቸዋለች፡፡ ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ነው፡፡ خَاشِعَةً أَ‍ب‍‍ْصَارُهُمْ تَرْهَقُهُمْ ذِلَّة‍‍‍ٌ ذَلِكَ ا‍لْيَوْمُ ا‍لَّذِي كَانُو‍‍ا‍ يُوعَد‍ُو‍نَ
Next Sūrah