52) Sūrat Aţ-Ţūr

Printed format

52) سُورَة الطُّور

Wa Aţūri 052-001 በጡር (ጋራ) እምላለሁ፡፡ وَالطّ‍‍ُ‍و‍ر‍ِ
Wa Kitābin Masţūrin 052-002 በተጻፈው መጽሐፍም፡፡ وَكِت‍‍َ‍ا‍ب‍‍‍ٍ مَسْط‍‍ُ‍و‍ر‍ٍ
Fī Raqqin Manshūrin 052-003 በተዘረጋ ብራና ላይ፤ (በተጻፈው)፡፡ فِي رَقّ‍‍‍ٍ مَ‍‍ن‍‍ْش‍‍ُ‍و‍ر‍ٍ
Wa Al-Bayti Al-Ma`mūri 052-004 በደመቀው ቤትም፡፡ وَالْبَيْتِ ا‍لْمَعْم‍‍ُ‍و‍ر‍ِ
Wa As-Saqfi Al-Marfū`i 052-005 ከፍ በተደረገው ጣራም፡፡ وَالسَّ‍‍ق‍‍ْفِ ا‍لْمَرْف‍‍ُ‍و‍عِ
Wa Al-Baĥri Al-Masjūri 052-006 በተመላው ባሕርም እምላለሁ፡፡ وَالْبَحْ‍‍ر‍ِ ا‍لْمَسْج‍‍ُ‍و‍ر‍ِ
'Inna `Adhāba Rabbika Lawāqi`un 052-007 የጌታህ ቅጣት በእርግጥ ወዳቂ ነው፤ (የማይቀር ነው)፡፡ إِ‍نّ‍‍َ عَذ‍َا‍بَ رَبِّكَ لَوَاقِع‍‍‍ٌ
Mā Lahu Min Dāfi`in 052-008 ለእርሱ ምንም ገፍታሪ የለውም፡፡ مَا لَهُ مِ‍‍ن‍ْ دَافِع‍‍‍ٍ
Yawma Tamūru As-Samā'u Mawrāan 052-009 ሰማይ ብርቱ መዞርን በምትዞርበት ቀን (ይኾናል)፡፡ يَوْمَ تَم‍‍ُ‍و‍رُ ا‍لسَّم‍‍َ‍ا‍ءُ مَوْرا‍ً
Wa Tasīru Al-Jibālu Sayrāan 052-010 ተራራዎችም መኼድን በሚኼዱበት (ቀን)፡፡ وَتَس‍‍ِ‍ي‍‍ر‍ُ ا‍لْجِب‍‍َ‍ا‍لُ سَيْرا‍ً
Fawaylun Yawma'idhin Lilmukadhdhibīna 052-011 ለአስተባባዮችም ያን ጊዜ ወዮላቸው፡፡ فَوَيْل‍‍‍ٌ يَوْمَئِذ‍ٍ لِلْمُكَذِّب‍‍ِ‍ي‍نَ
Al-Ladhīna HumKhawđin Yal`abūna 052-012 ለእነዚያ እነርሱ በውሸት ውስጥ የሚጫወቱ ለኾኑት፡፡ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ هُمْ فِي خَوْض‍‍‍ٍ يَلْعَب‍‍ُ‍و‍نَ
Yawma Yuda``ūna 'Ilá Nāri Jahannama Da``āan 052-013 ወደ ገሀነም እሳት በኀይል መግገፍተርን በሚግገፈተሩበት ቀን፡፡ يَوْمَ يُدَعّ‍‍ُ‍و‍نَ إِلَى ن‍‍َ‍ا‍ر‍ِ جَهَ‍‍ن‍ّ‍‍َمَ دَعّا‍ً
Hadhihi An-Nāru Allatī Kuntum Bihā Tukadhdhibūna 052-014 ይህቺ ያቺ በእርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁት እሳት ናት፡፡ هَذِهِ ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َ‍ا‍رُ ا‍لَّتِي كُ‍‍ن‍تُ‍‍م‍ْ بِهَا تُكَذِّب‍‍ُ‍و‍نَ
'Afasiĥrun Hādhā 'Am 'Antum Lā Tubşirūna 052-015 ይህ (ፊት ትሉ እንደነበራችሁት) ድግምት ነውን? ወይስ እናንተ አታዩምን? أَفَسِحْرٌ هَذَا أَمْ أَ‍ن‍‍ْتُمْ لاَ تُ‍‍ب‍‍ْصِر‍ُو‍نَ
Aşlawhā Fāşbirū 'Aw Lā Taşbirū Sawā'un `Alaykum 'Innamā Tujzawna Mā Kuntum Ta`malūna 052-016 ግቧት ታገሱም ወይም አትታገሡ በእናንተ ላይ እኩል ነው፡፡ የምትምመነዱት ትሠሩት የነበራችሁትን (ፍዳ) ብቻ ነው (ይባላሉ)፡፡ ا‍صْلَوْهَا فَاصْبِرُو‍ا‍ أَوْ لاَ تَصْبِرُوا‍ سَو‍َا‍ءٌ عَلَيْكُمْ إِ‍نّ‍‍َمَا تُ‍‍ج‍‍ْزَوْنَ مَا كُ‍‍ن‍تُمْ تَعْمَل‍‍ُ‍و‍نَ
'Inna Al-Muttaqīna Fī Jannātin Wa Na`īmin 052-017 አላህን ፈሪዎቹ በእርግጥ በገነቶችና በጸጋ ውስጥ ናቸው፡፡ إِ‍نّ‍‍َ ا‍لْمُتَّق‍‍ِ‍ي‍نَ فِي جَ‍‍ن‍ّ‍‍َ‍ا‍ت‍‍‍ٍ وَنَع‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٍ
Fākihīna Bimā 'Ātāhum Rabbuhum Wa Waqāhum Rabbuhum `Adhāba Al-Jaĥīmi 052-018 ጌታቸው በሰጣቸው ጸጋ ተደሳቾች ኾነው (በገነት ውስጥ ናቸው)፡፡ የገሀነምንም ስቃይ ጌታቸው ጠበቃቸው፡፡ فَاكِه‍‍ِ‍ي‍نَ بِمَ‍‍ا آتَاهُمْ رَبُّهُمْ وَوَقَاهُمْ رَبُّهُمْ عَذ‍َا‍بَ ا‍لْجَح‍‍ِ‍ي‍مِ
Kulū Wa Ashrabū Hanī'āan Bimā Kuntum Ta`malūna 052-019 آ«ትሠሩት በነበራችሁት ምክንያት ተደሳቾች ኾናችሁ ብሉ፤ ጠጡም፤آ» (ይባላሉ)፡፡ كُلُو‍‍ا‍ وَا‍شْرَبُو‍‍ا‍ هَن‍‍ِ‍ي‍ئا‍ً بِمَا كُ‍‍ن‍تُمْ تَعْمَل‍‍ُ‍و‍نَ
Muttaki'īna `Alá Sururin Maşfūfatin Wa Zawwajnāhum Biĥūrin `Īnin 052-020 በተደረደሩ አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ኾነው (በገነት ይኖራሉ)፡፡ ዓይናማዎች በኾኑ ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡ مُتَّكِئ‍‍ِ‍ي‍نَ عَلَى سُرُر‍ٍ مَصْفُوفَة‍‍‍ٍ وَزَوَّ‍‍ج‍‍ْنَاهُ‍‍م‍ْ بِح‍‍ُ‍و‍رٍ ع‍‍ِ‍ي‍ن‍‍‍ٍ
Wa Al-Ladhīna 'Āmanū Wa Attaba`at/hum Dhurrīyatuhum Bi'īmānin 'Alĥaqnā Bihim Dhurrīyatahum Wa Mā 'Alatnāhum Min `Amalihim Min Shay'in Kullu Amri'in Bimā Kasaba Rahīnun 052-021 እነዚያም ያመኑትና ዝርያቸውም በእምነት የተከተለቻቸው ዝርያቸውን በእነርሱ እናስጠጋለን፡፡ ከሥራቸውም ምንም አናጎድልባቸውም፡፡ ሰው ሁሉ በሠራው ሥራ ተያዢ ነው፡፡ وَالَّذ‍ِي‍نَ آمَنُو‍‍ا‍ وَا‍تَّبَعَتْهُمْ ذُرِّيَّتُهُ‍‍م‍ْ بِإِيم‍‍َ‍ا‍نٍ أَلْحَ‍‍ق‍‍ْنَا بِهِمْ ذُرِّيَّتَهُمْ وَمَ‍‍ا‍ أَلَتْنَاهُ‍‍م‍ْ مِنْ عَمَلِهِ‍‍م‍ْ مِ‍‍ن‍ْ شَيْء‍ٍ كُلُّ ا‍مْ‍‍ر‍‍ِئ‍‍‍ٍ بِمَا كَسَبَ رَه‍‍ِ‍ي‍ن‍‍‍ٌ
Wa 'Amdadnāhum Bifākihatin Wa Laĥmin Mimmā Yashtahūna 052-022 ከሚሹትም ሁሉ እሸትንና ስጋን እንጨምርላቸዋለን፡፡ وَأَمْدَ‍د‍‍ْنَاهُ‍‍م‍ْ بِفَاكِهَة‍‍‍ٍ وَلَحْم‍‍‍ٍ مِ‍‍م‍ّ‍‍َا يَشْتَه‍‍ُ‍و‍نَ
Yatanāza`ūna Fīhā Ka'sāan Lā Laghwun Fīhā Wa Lā Ta'thīmun 052-023 በውስጧ መጠጥን ይሰጣጣሉ፡፡ በውስጧ ውድቅ ንግግርና መውወንጀልም የለም፡፡ يَتَنَازَع‍‍ُ‍و‍نَ فِيهَا كَأْسا‍ً لاَ لَغْو‍ٌ فِيهَا وَلاَ تَأْث‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٌ
Wa Yaţūfu `Alayhim Ghilmānun Lahum Ka'annahum Lu'ulu'uun Maknūnun 052-024 ለነርሱም የኾኑ ወጣቶች ልክ የተሸፈነ ሉል መስለው በእነርሱ ላይ (ለማሳለፍ) ይዘዋወራሉ፡፡ وَيَط‍‍ُ‍و‍فُ عَلَيْهِمْ غِلْم‍‍َ‍ا‍ن‍‍‍ٌ لَهُمْ كَأَ‍نّ‍‍َهُمْ لُؤْلُؤ‍ٌ مَكْن‍‍ُ‍و‍ن‍‍‍ٌ
Wa 'Aqbala Ba`đuhum `Alá Ba`đin Yatasā'alūna 052-025 የሚጠያየቁ ኾነውም ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይዞራል፡፡ وَأَ‍ق‍‍ْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَى بَعْض‍‍‍ٍ يَتَس‍‍َ‍ا‍ءَل‍‍ُ‍و‍نَ
Qālū 'Innā Kunnā Qablu Fī 'Ahlinā Mushfiqīna 052-026 آ«እኛ ፊት በቤተሰቦቻችን ውስጥ (ከቅጣት) ፈሪዎች ነበርንآ» ይላሉ፡፡ قَالُ‍‍و‍‍ا‍ إِ‍نّ‍‍َا كُ‍‍ن‍ّ‍‍َا قَ‍‍ب‍‍ْلُ فِ‍‍ي‍ أَهْلِنَا مُشْفِق‍‍ِ‍ي‍نَ
Famanna Al-Lahu `Alaynā Wa Waqānā `Adhāba As-Samūmi 052-027 آ«አላህም በእኛ ላይ ለገሰ፡፡ የመርዛም እሳት ቅጣትንም ጠበቀን፡፡ فَمَ‍‍ن‍ّ‍‍َ ا‍للَّهُ عَلَيْنَا وَوَقَانَا عَذ‍َا‍بَ ا‍لسَّم‍‍ُ‍و‍مِ
'Innā Kunnā Min Qablu Nad`ūhu 'Innahu Huwa Al-Barru Ar-Raĥīmu 052-028 آ«እኛ ከዚህ በፊት እንለምነው ነበርን፡፡ እነሆ እርሱ በጎ ዋይ አዛኝ ነውናآ» (ይላሉ)፡፡ إِ‍نّ‍‍َا كُ‍‍ن‍ّ‍‍َا مِ‍‍ن‍ْ قَ‍‍ب‍‍ْلُ نَ‍‍د‍‍ْع‍‍ُ‍و‍هُ إِ‍نّ‍‍َهُ هُوَ ا‍لْبَرُّ ا‍لرَّح‍‍ِ‍ي‍مُ
Fadhakkir Famā 'Anta Bini`mati Rabbika Bikāhinin Wa Lā Majnūnin 052-029 (ሰዎችን) አስታውስም፡፡ አንተም በጌታህ ጸጋ ምክንያት ጠንቋይም ዕብድም አይደለህም፡፡ فَذَكِّرْ فَمَ‍‍ا‍ أَ‍ن‍‍ْتَ بِنِعْمَةِ رَبِّكَ بِكَاهِن‍‍‍ٍ وَلاَ مَ‍‍ج‍‍ْن‍‍ُ‍و‍ن‍‍‍ٍ
'Am Yaqūlūna Shā`irun Natarabbaşu Bihi Rayba Al-Manūni 052-030 ይልቁንም የሞትን አደጋ በእርሱ የምንጠባበቅበት የኾነ ባለ ቅኔ ነው ይላሉን? أَمْ يَقُول‍‍ُ‍و‍نَ شَاعِر‍ٌ نَتَرَبَّصُ بِهِ رَيْبَ ا‍لْمَن‍‍ُ‍و‍نِ
Qul Tarabbaşū Fa'innī Ma`akum Mina Al-Mutarabbişīna 052-031 آ«ተጠባበቁ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝآ» በላቸው፡፡ قُلْ تَرَبَّصُو‍‍ا‍ فَإِ‍نّ‍‍ِي مَعَكُ‍‍م‍ْ مِنَ ا‍لْمُتَرَبِّص‍‍ِ‍ي‍نَ
'Am Ta'muruhum 'Aĥlāmuhum Bihadhā 'Am Hum Qawmun Ţāghūna 052-032 አእምሮዎቻቸው በዚህ ያዟቸዋልን? አይደለም በእውነቱ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦች ናቸው፡፡ أَمْ تَأْمُرُهُمْ أَحْلاَمُهُ‍‍م‍ْ بِهَذَا أَمْ هُمْ قَوْم‍‍‍ٌ طَاغ‍‍ُ‍و‍نَ
'Am Yaqūlūna Taqawwalahu Bal Lā Yu'uminūna 052-033 ወይም آ«ቀጠፈው ይላሉን?آ» አይደለም፤ በእውነቱ አያምኑም፡፡ أَمْ يَقُول‍‍ُ‍و‍نَ تَقَوَّلَهُ بَ‍‍ل لاَ يُؤْمِن‍‍ُ‍و‍نَ
Falya'tū Biĥadīthin Mithlihi 'In Kānū Şādiqīna 052-034 እውነተኞችም ቢኾኑ መሰሉ የኾነን ንግግር ያምጡ፡፡ فَلْيَأْتُو‍‍ا‍ بِحَد‍ِي‍ث‍‍‍ٍ مِثْلِهِ إِ‍ن‍ْ كَانُو‍‍ا‍ صَادِق‍‍ِ‍ي‍نَ
'Am Khuliqū Min Ghayri Shay'in 'Am Humu Al-Khāliqūna 052-035 ወይስ ያለ አንዳች (ፈጣሪ) ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን? أَمْ خُلِقُو‍‍ا‍ مِنْ غَيْ‍‍ر‍ِ شَيْءٍ أَمْ هُمُ ا‍لْخَالِق‍‍ُ‍و‍نَ
'Am Khalaqū As-Samāwāti Wa Al-'Arđa Bal Lā Yūqinūna 052-036 ወይስ ሰማያትንና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም አያረጋግጡም፡፡ أَمْ خَلَقُو‍‍ا‍ ا‍لسَّمَاو‍َا‍تِ وَا‍لأَرْضَ بَ‍‍ل لاَ يُوقِن‍‍ُ‍و‍نَ
'Am `Indahum Khazā'inu Rabbika 'Am Humu Al-Musayţirūna 052-037 ወይስ የጌታህ ግምጃ ቤቶች እነርሱ ዘንድ ናቸውን? ወይስ እነርሱ አሸናፊዎች ናቸውን? أَمْ عِ‍‍ن‍‍ْدَهُمْ خَز‍َا‍ئِنُ رَبِّكَ أَمْ هُمُ ا‍لْمُسَيْطِر‍ُو‍نَ
'Am Lahum Sullamun Yastami`ūna Fīhi Falya'ti Mustami`uhum Bisulţānin Mubīnin 052-038 ወይስ ለእነርሱ በእርሱ ላይ (ከሰማይ) የሚያዳምጡበት መሰላል አላቸውን? አድማጫቸውም (ሰማሁ ቢል) ግልጽን አስረጅ ያምጣ፡፡ أَمْ لَهُمْ سُلَّم‍‍‍ٌ يَسْتَمِع‍‍ُ‍و‍نَ ف‍‍ِ‍ي‍هِ فَلْيَأْتِ مُسْتَمِعُهُ‍‍م‍ْ بِسُلْط‍‍َ‍ا‍ن‍‍‍ٍ مُب‍‍ِ‍ي‍ن‍‍‍ٍ
'Am Lahu Al-Banātu Wa Lakumu Al-Banūna 052-039 ወይስ ለእርሱ ሴቶች ልጆች አሉትን? ለእናንተም ወንዶች ልጆች አሏችሁን? أَمْ لَهُ ا‍لْبَن‍‍َ‍ا‍تُ وَلَكُمُ ا‍لْبَن‍‍ُ‍و‍نَ
'Am Tas'aluhum 'Ajrāan Fahum Min Maghramin Muthqalūna 052-040 ወይስ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳው የተከበዱ ናቸውን? أَمْ تَسْأَلُهُمْ أَ‍ج‍‍ْرا‍ً فَهُ‍‍م‍ْ مِ‍‍ن‍ْ مَغْرَم‍‍‍ٍ مُثْقَل‍‍ُ‍و‍نَ
'Am `Indahumu Al-Ghaybu Fahum Yaktubūna 052-041 ወይስ ሩቁ ምስጢር እነርሱ ዘንድ ነውን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን? أَمْ عِ‍‍ن‍‍ْدَهُمُ ا‍لْغَيْبُ فَهُمْ يَكْتُب‍‍ُ‍و‍نَ
'Am Yurīdūna Kaydāan Fa-Al-Ladhīna Kafarū Humu Al-Makīdūna 052-042 ወይስ ተንኮልን (ባንተ) ይሻሉን? እነዚያም የካዱት እነርሱ በተንኮል ተሸናፊዎች ናቸው፡፡ أَمْ يُ‍‍ر‍‍ِيد‍ُو‍نَ كَيْدا‍ً فَالَّذ‍ِي‍نَ كَفَرُوا‍ هُمُ ا‍لْمَكِيد‍ُو‍نَ
'Am Lahum 'Ilahun Ghayru Al-Lahi Subĥāna Al-Lahi `Ammā Yushrikūna 052-043 ወይስ ለእነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ አላቸውን? አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡ أَمْ لَهُمْ إِلَهٌ غَيْرُ ا‍للَّهِ سُ‍‍ب‍‍ْح‍‍َ‍ا‍نَ ا‍للَّهِ عَ‍‍م‍ّ‍‍َا يُشْ‍‍ر‍‍ِك‍‍ُ‍و‍نَ
Wa 'In Yaraw Kisfāan Mina As-Samā'i Sāqiţāan Yaqūlū Saĥābun Markūmun 052-044 ከሰማይም ቁራጭን (በእነርሱ ላይ) ወዳቂ ኾኖ ቢያዩ ኖሮ آ«ይህ የተደራረበ ደመና ነውآ» ይሉ ነበር፡፡ وَإِ‍ن‍ْ يَرَوْا كِسْفا‍ً مِنَ ا‍لسَّم‍‍َ‍ا‍ءِ سَاقِطا‍ً يَقُولُو‍‍ا‍ سَح‍‍َ‍ا‍ب‍‍‍ٌ مَرْك‍‍ُ‍و‍م‍‍‍ٌ
Fadharhum Ĥattá Yulāqū Yawmahumu Al-Ladhī Fīhi Yuş`aqūna 052-045 ያንንም በእርሱ የሚግገደሉበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ فَذَرْهُمْ حَتَّى يُلاَقُو‍‍ا‍ يَوْمَهُمُ ا‍لَّذِي ف‍‍ِ‍ي‍هِ يُصْعَق‍‍ُ‍و‍نَ
Yawma Lā Yughnī `Anhum Kayduhum Shay'āan Wa Lā Hum Yunşarūna 052-046 ተንኮላቸው ከእነርሱ ምንንም የማይጠቅማቸውንና እነርሱም የማይርረዱበትን ቀን (እስከ ሚገናኙ ተዋቸው)፡፡ يَوْمَ لاَ يُغْنِي عَنْهُمْ كَيْدُهُمْ شَيْئا‍ً وَلاَ هُمْ يُ‍‍ن‍صَر‍ُو‍نَ
Wa 'Inna Lilladhīna Žalamū `Adhābāan Dūna Dhālika Wa Lakinna 'Aktharahum Lā Ya`lamūna 052-047 ለእነዚያ ለበደሉትም ከዚህ ሌላ ቅርብ ቅጣት አልላቸው፡፡ ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም፡፡ وَإِ‍نّ‍‍َ لِلَّذ‍ِي‍نَ ظَلَمُو‍‍ا‍ عَذَابا‍ً د‍ُو‍نَ ذَلِكَ وَلَكِ‍‍ن‍ّ‍‍َ أَكْثَرَهُمْ لاَ يَعْلَم‍‍ُ‍و‍نَ
Wa Aşbir Liĥukmi Rabbika Fa'innaka Bi'a`yuninā Wa Sabbiĥ Biĥamdi Rabbika Ĥīna Taqūmu 052-048 ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፡፡ አንተ በጥበቃችን ውስጥ ነህና፡፡ ጌታህንም በምትነሳ ጊዜ ከማመስገን ጋር አወድሰው፡፡ وَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ فَإِ‍نّ‍‍َكَ بِأَعْيُنِنَا وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ ح‍‍ِ‍ي‍نَ تَق‍‍ُ‍و‍مُ
Wa Mina Al-Layli Fasabbiĥhu Wa 'Idbāra An-Nujūmi 052-049 ከሌሊቱም አወድሰው፡፡ በከዋክብት መዳበቂያ ጊዜም (ንጋት ላይ አወድሰው)፡፡ وَمِنَ ا‍للَّيْلِ فَسَبِّحْهُ وَإِ‍د‍‍ْب‍‍َ‍ا‍رَ ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍ُج‍‍ُ‍و‍مِ
Next Sūrah